የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

የሲዳማ መሶብ የአንድ ማእከል አገልግሎት ለመልካም አስተዳደር ችግሮች መፍትሔ እየሰጠ ነው

Apr 3, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ሃዋሳ፤ መጋቢት 24/2018(ኢዜአ)፦ የሲዳማ መሶብ የአንድ ማእከል አገልግሎት ለመልካም አስተዳደር ችግሮች መፍትሄ እየሰጠ መሆኑን የይርጋለም ከተማ ተገልጋዮች ገለጹ፡፡

መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ቴክኖሎጂ የተለያዩ የመንግሥት ተቋማትን አገልግሎቶች በአንድ ዲጂታል ሥርዓት በማቀናጀት፣ ደንበኞች እንደ መንጃ ፈቃድ፣ መታወቂያ እና የባንክ አገልግሎቶችን በአንድ ቦታ በቀላሉ እንዲያገኙ ያስችላል።

በሲዳማ መሶብ የአንድ ማእከል አገልግሎትም 17 ተቋማት የገቡ ሲሆን ከ74 በላይ አገልግሎቶች እየተሰጡ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

የማእከሉ ተገልጋዮች ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ በቴክኖሎጂ የታገዘው የማእከሉ አገልግሎት ጊዜ፣ ወጪንና እንግልት የቀነሰና ለመልካም አስተዳደር ችግሮች መፍትሄን የሰጠ ነው፡፡


ከአስተያየት ሰጪዎቹ መካከል የይርጋለም ከተማ ነዋሪው አቶ ከበደ አመሎ የመጡበትን ጉዳይ በአስር ደቂቃ ውስጥ መፈጸማቸውን ጠቅሰው ከዚህ ቀደም የነበረው አሰራር የተንዛዛ እንደነበረ አስታውሰዋል፡፡

አገልግሎቱ በዲጂታል የታገዘ መሆኑና የተለያዩ ተቋማት በአንድ ቦታ መገኘታቸው የተገልጋዩን እንግልት ለመቀነስና ፈጣን አገልግሎት እንዲያገኙ ማስቻሉን ተናግረዋል፡፡

የማእከሉ አገልግሎት የተገልጋይ እርካታን ከማሳደግ ባለፈ ሀገራዊ ፋይዳው ከፍተኛ መሆኑን የጠቀሱት አስተያየት ሰጪው የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታት በመንግስትና ህዝብ መካከልም መተማመን ይፈጥራል ነው ያሉት፡፡

ሌላኛው ተገልጋይ አቶ ዎማ ጋቢሶ በበኩላቸው ውክልና ለመስጠት ወደ ማእከሉ መምጣታቸውን ጠቅሰው በተቋሙ የተፈጠረው አዲስ የስራ እሳቤ የተገልጋዩን ጊዜ፣ ወጪና እንግልት ከመቀነስ ባለፈ በእውቀት እንዲገለገል አስችሏል ብለዋል፡፡


ስለሚያገኙት አገልግሎት የህግ ድጋፍ ጭምር ማግኘታቸውን ጠቅሰው አገልግሎቱ በቴክኖሎጂ የታገዘ መሆኑና የተለያዩ ተቋማት በአንድ ላይ መኖራቸው አገልግሎቱን ቀልጣፋ እንዳደረገው ተናግረዋል፡፡

በማእከሉ የሚሰጠው አገልግሎት ፍትሃዊና ከዚህ ቀደም ለሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮች መፍትሄን ያመላከተ በመሆኑ ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

በማእከሉ የሚሰጠው አገልግሎት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ በመሆኑ ቀልጣፋ አገልግሎት ማግኘታቸውን የገለጹት ወይዘሮ መታሰቢያ አለማየሁ በበኩላቸው በአገልግሎት አሰጣጡ ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡


የማእከሉ መከፈት ከዚህ ቀደም ረጅም ጊዜ ወስዶ ይሰጥ የነበረውን አገልግሎት በ15 ደቂቃ ውስጥ መፈጸም በመቻላቸው ጊዜ፣ ወጪና እንግልትን ቀንሶላቸዋል፡፡

የሲዳማ መሶብ የአንድ ማእከል አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ እንግዳየሁ ዘውዴ በማእከሉ 17 ተቋማት መኖራቸውንና 74 አገልግሎቶች እየተሰጡ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

እስካሁን ከ35 ሺህ ለሚበልጡ ዜጎች አገልግሎት መሰጠቱን የጠቀሱት ዳይሬክተሩ የተገልጋዮች እርካታን ለመፈተሽ በተደረገው የዳሰሳ ጥናት ተግባሩ ውጤታማ መሆኑን ገልጸዋል፡፡


መሶብ የአንድ ማእከል አገልግሎት ከዚህ ቀደም በአገልግሎቱ ዘርፍ የሚታዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመቅረፍ በመንግስትና ህዝብ መካከል መተማመን እንዲፈጠር እያስቻለ ነው ብለዋል፡፡

በቀጣይም በክልሉ በሚገኙ ሰባት ከተማ አስተዳደሮችና በሃዋሳ ከተማ ተጨማሪ ማዕከል በማቋቋም አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ እቅድ ተነድፎ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የሲዳማ መሶብ የአንድ ማእከል አገልግሎት መስከረም 15/2018 ዓ.ም ተመርቆ በይፋ ወደ አገልግሎት መግባቱ ይታወቃል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የማዕከል ወደ ሥራ መግባት በክልሉ የሚገኘውን ሰፊ የእንስሳት ሀብት ወደ ላቀ የኢኮኖሚ ጥቅም ለመለወጥ ያስችላል

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፦ የአፋር ሰመራ ሁለተኛ ደረጃ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ወደ ሥራ መግባቱ በክልሉ የሚገኘውን ሰፊ የእንስሳት ሀ...

Apr 1, 2026

<p>ተቋማት ራሳቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ ይገባል- ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...

Feb 28, 2025

<p>በክልሉ የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች እየተከናወኑ ነው</p>

ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...

Feb 28, 2025

<p>ተቋማቱ በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...

Feb 28, 2025