
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለጹ።
ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን ከክልሉ ከፍተኛ የመንግስት እና የፓርቲ አመራሮች ጋር በመሆን ዕድሳት የተደረገለትን የክልሉን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ጎብኝተዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በመስክ ምልከታው ወቅት እንደገለፁት የብልፅግና ፓርቲ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አመራር ሰጪነት አዳዲስ እሳቤዎችን ተግባራዊ በማድረግ በህዝብ ዘንድ ተቀባይነትን ያገኙ አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል።
በተለይ ከግቢ እስከ አገር በሚል እሳቤ ፅዳትን፤ውበትን እና ምቾትን መሰረት ያደረጉ ተግባራትን በማከናወን ለዜጎች፤ቱሪስቶች እና ሰራተኞች ምቹ የመኖሪያ እና የስራ አካባቢዎችን ለመፍጠር እየተሰራ ነው ብለዋል።
ይህንን መነሻ በማድረግም በክልሉ በሚከናወኑ የኮሪደር ልማቶች የሐረር ከተማን የማስዋብ፤ንፁህ እና ምቹ የማድረግ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኝ አመልክተዋል።
ዕድሳት የተደረገለት የሐረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ፕሮጀክትም የዚሁ ማሳያ መሆኑን ነው የገለጹት።
ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት ጎን ለጎን ተቋማቸውን ለተገልጋይ የተመቹ ውብ እና ፅዱ ማድረግ እንደሚገባቸው አሳስበዋል።
በተለይም ተቋማት መሰረተ ልማቶችን ጨምሮ የተገልጋይ ማረፊያዎች ማሟላት እንዳለባቸው ገልጸዋል።
በብልፅግና ፓርቲ የሐረሪ ክልል ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ በበኩላቸው ፓርቲው ተቋማትን ፅዱ፤ውብ እና ምቹ በማድረግ ያመጣውን ልምድ በመተግበር ውጤት ማስመዝገብ እንደሚገባ አመልክተዋል።
ዕድሳት የተደረገለት የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ህንፃም ይህንን መነሻ አድርጎ መከናወኑንና መሰል ተግባራትን በዘላቂነት ማስቀጠል እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
በቀጣይም ፅህፈት ቤቱን በአስፈላጊው የሰው ኃይል እና ግብዓት በማደራጀት የተቋቋመለትን አላማ እና ግብ እንዲያሳካ በትኩረት ይሰራል ማለታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
አቶ ጌቱ ለፅህፈት ቤቱ ህንፃ ዕድሳት ድጋፍ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
በጉብኝቱ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ፣ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ፣የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ሱልጣን አብዱሰላም ፣ የሀረሪ ብሄራዊ ጉባኤ አፈ ጉባኤ አቶ ሙህየዲን አህመድ ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ ሮዛ ኡመርን ጨምሮ የክልሉ የመንግስትና የፓርቲ አመራሮች ተገኝተዋል።
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 11/2018 (ኢዜአ)፦ የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ መገንባት መንግሥት የኢንዱስትሪው ዘርፍ ለሀገር ያለውን አበርክቶ ለማሳደግ በፖሊሲና ...
May 20, 2026
ድሬዳዋ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ውጤታማ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠላቸውን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ...
May 7, 2026
ደብረ ማርቆስ ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ የደብረ ማርቆስ ከተማን ባህል፣ ታሪክ ፣ ቅርስና ማህበራዊ እሴት በመጠበቅና በማልማት ለቱሪስት መስህብነት ለማዋ...
May 7, 2026
በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የአቪዬሽን ታሪክ ታይቶ የማይታወቅና በአህጉሪቱ ትልቁ የሆነውን የ12 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ግዙፍ የኤርፖርት ግንባታ ፕሮጀክት...
Apr 24, 2026