🔇Unmute
ሮቤ ፤መጋቢት 22/2018(ኢዜአ)፡-በለውጡ ዓመታት ተግባራዊ የተደረገው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ የዘርፉን ስብራት በመጠገን ሁለንተናዊ እድገት ማምጣት ያስቻለ መሆኑን የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሃብት ምሁራን ገለጹ።
መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም ወደ ስልጣን የመጣው የለውጡ መንግስት የኢትዮጵያን የምጣኔ ሃብት መዋቅራዊ ችግር በመፍታትና የዘርፉን ስብራት በመጠገን ዘላቂና ቀጣይነት ያለው እድገት ማምጣት አስችሏል።
ከዚሁ ጋር በተገናኘ ኢዜአ ያነጋገራቸው በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስና ቢዝነስ ኮሌጅ ዲንና የዘርፉ ተመራማሪ ጌታሁን ቶሎሳ (ዶ/ር)፤ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው በኢትዮጵያ የነበሩ ውስብስብ ችግሮችን መፍታትና ትክክለኛ የእድገት አቅጣጫ እንድትከተል ያደረገ ነው ብለዋል።
የተሟላ የማክሮ-ኢኮኖሚ ማሻሻያውም የዋጋ ንረትን መቆጣጠር፣ የውጭ ምንዛሬ ተመን ማስተካከል እና የመንግስት ዕዳን ማስተዳደር ያስቻለ ትልቅ እርምጃ ስለመሆኑ አስረድተዋል።
የመዋቅር ማሻሻያ ማድረግ ሌላኛው የማሻሻያ ምሰሶ ሲሆን፣ ይህም የንግድ አካባቢን ምቹ በማድረግ ምርታማነትን መጨመር፣ የኢንቨስትመንት ከባቢን ማሻሻል እና የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታን ማጠናከር ያስቻለ መሆኑን አንስተዋል።
በተለይ ከዚህ በፊት በግብርና ክፍለ ኢኮኖሚ ላይ ብቻ ተወስኖ የቆየውን እሳቤ ወደ ብዝኃ-ኢኮኖሚ ሪፎርም እንዲቀየር ማድረጉ በሁሉም መስክ ከፍተኛ መነቃቃት እንዲፈጠር ማስቻሉን አመልክተዋል።
በግብርና ዘርፍ የመደበኛ ግብርና ልማት ስራን ውጤታማ ከማድረግ ባለፈ፣ የመስኖ ልማት ስራ ኢትዮጵያ በስንዴ ራሷን እንድትችል ዕድል የፈጠረ መሆኑን ተናግረዋል።
ማኑፋክቸሪንግ፣ ማዕድን እና ቱሪዝም ዘርፎች የተሰሩ ስራዎችም ኢትዮጵያ ቀጣይነት ያለው የእድገት ጉዞ ላይ እንድትገኝ ያስቻለ መሆኑን ጠቁመዋል።
በዚህም ሪፎርሙ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በሙሉ አቅም በመጠቀም፣ በስራ እድል ፈጠራና የዜጎችን የኑሮ ደረጃ በማሻሻል ረገድ ለውጥ ማስመዝገቡን በማሳያነት አንስተዋል።
በለውጡ ዓመታት ተግባራዊ የተደረገው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው የዘርፉን ስብራት በመጠገን ኢትዮጵያ በትክክለኛ የእድገት አቅጣጫ እንድትግዝ ያስቻለ መሆኑን ገልጸዋል።
በዩኒቨርሲቲው የማርኬቲንግ ማኔጅመንት መምህርና ተመራማሪ አዲስ በቀለ፤ በኢትዮጵያ ተግባራዊ የተደረገው ብዝኃ-ዘርፍ የኢኮኖሚ ሪፎርም ሀገሪቷን ከውድቀት የታደገ ትክክለኛ መፍትሄ መሆኑን አስረድተዋል።
የመንግስት በገበያ ላይ የተመሰረተ የተረጋጋ የውጭ ምንዛሬ ተመን እንዲኖር ማስቻሉ ከማሳያዎቹ መካከል መሆኑን ጠቅሰዋል።
ሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሸያው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት ዘላቂና ቀጣይነት ያለው ማድረግ ያስቻለስለመሆኑም አስረድተዋል።
በዚህ ረገድ የተጀመሩ በጎ ውጤቶች ዘላቂ እንዲሆኑ ዘርፉን በአግባቡ ከመምራት ባለፈ አስቻይ ሁኔታዎችን ማጠናከር ይገባል ብለዋል።
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 11/2018 (ኢዜአ)፦ የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ መገንባት መንግሥት የኢንዱስትሪው ዘርፍ ለሀገር ያለውን አበርክቶ ለማሳደግ በፖሊሲና ...
May 20, 2026
ድሬዳዋ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ውጤታማ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠላቸውን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ...
May 7, 2026
ደብረ ማርቆስ ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ የደብረ ማርቆስ ከተማን ባህል፣ ታሪክ ፣ ቅርስና ማህበራዊ እሴት በመጠበቅና በማልማት ለቱሪስት መስህብነት ለማዋ...
May 7, 2026
በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የአቪዬሽን ታሪክ ታይቶ የማይታወቅና በአህጉሪቱ ትልቁ የሆነውን የ12 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ግዙፍ የኤርፖርት ግንባታ ፕሮጀክት...
Apr 24, 2026