🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ በኢትዮጵያ እና ጣሊያን መካከል ያለውን የኢንቨስትመንት ፍሰት በዓይነትና በመጠን ከፍተኛ ዕድገት እንዲመዘገብ ማስቻሉን የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ገለጹ።
የመጀመሪያው የኢትዮ-ጣሊያን የኮንስትራክሽን፣ የመሰረተ ልማትና የከተማ ልማት ፎረም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡

በወቅቱ ንግግር ያደረጉት የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ፤ ኢትዮጵያ ተግባራዊ እያደረገች ያለችው ሁሉን አቀፍ ሪፎርም ለዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንት ምቹና ሳቢ ምህዳር ፈጥሯል ብለዋል።
ይህ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ በኢትዮጵያ እና በጣሊያን መካከል ያለውን የኢንቨስትመንት ትስስር በተለያዩ ዘርፎች በዓይነትም ሆነ በመጠን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲያድግ ማድረጉን አብራርተዋል።
የጣሊያን ባለሀብቶች በኢትዮጵያ በኮንስትራክሽን፣ በማሽነሪ አቅርቦትና በሌሎች ልዩ ልዩ የኢንቨስትመንት መስኮች በመሰማራት ተጨባጭ ውጤት እያስመዘገቡ መሆኑን ጠቁመዋል።
የተጀመረው ፎረምም በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች የሚሰማሩ የጣሊያን ባለሀብቶችን ቁጥር ይበልጥ እንደሚያሳድገው ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
ይህ የሁለቱን ሀገራት ትብብር ከኢኮኖሚ ባለፈ በልማትና በሌሎችም ዘርፎች ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑንም ጠቅሰዋል።
ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎችን የሚስብ የመሰረተ ልማትና የአሰራር ስርዓት እየገነባች መሆኑን ጠቅሰው በተለይም አዲስ አበባ በውጭ ኢንቨስተሮች ዘንድ ተመራጭ መዳረሻ እየሆነች መምጣቷን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በርካታ የህዝብ ቁጥር ያላት፣ ምቹ የገበያ ዕድልና መንግስታዊ ክትትል የማይለየው ቀልጣፋ አገልግሎት የሚሰጥባት ሀገር በመሆኗ፣ የቀጣናው መሪ የኢንቨስትመንት መዳረሻነቷን አጠናክራ መቀጠሏን አስረድተዋል።
እንዲሁም ኢትዮጵያ የቀጣናው የልማት፣ የሰላምና የደህንነት ማዕከል ሆና እንደምትቀጥልና የሁለቱ ሀገራት ዘላቂ ትብብርም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር ሴም ፋብሪዚ በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ እና ጣሊያን የታሪካዊና የረጅም ጊዜ ትብብር ባለቤቶች መሆናቸውን አስታውሰዋል።
ሁለቱ ሀገራት በተለያዩ ዘርፎች የጋራ ራዕይ እንዳላቸው ጠቁመው፤ ይህ ፎረም ትብብራቸውን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ገልጸዋል።
በአዲስ አበባ የታየው የመሰረተ ልማት ዕድገት የሚደነቅ መሆኑን ጠቅሰው ይህንንም ተዘዋውረው መመልከታቸውን አክለዋል፡፡
ለከተማዋ ሁሉን አቀፍ ዕድገት ጣሊያን የበኩሏን ሚና እየተወጣች መሆኑንና በቀጣይም ትብብሩን ለማጠናከር በትጋት እንደምትሰራ አረጋግጠዋል።
በፎረሙ መክፈቻ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር አብርሃም በላይ(ዶ/ር)፣ የጣሊያን የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ምክትል ሚኒስትር ማሪያ ትሪፖዲ፣ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ የትምጌታ አስራት(ዶ/ር)፣ በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር ሴም ፋብሪዚ እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፦ የአፋር ሰመራ ሁለተኛ ደረጃ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ወደ ሥራ መግባቱ በክልሉ የሚገኘውን ሰፊ የእንስሳት ሀ...
Apr 1, 2026
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025