
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 22/2017(ኢዜአ)፦ ዛምቢያ እና ሞዛምቢክ ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ኢኒሼቲቭና በሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር ካስመዘገበችው ስኬት ልምድ መቅሰም እንደሚፈልጉ ገልጸዋል።
የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ(ዶ/ር) በአዲስ አበባ እየተካሄደ ካለው ሁለተኛው የተመድ የምግብ ሥርዓት ጉባኤ በተጓዳኝ የሁለትዮሽ ውይይቶችን አድርገዋል።

ሚኒስትር ግርማ አመንቴ(ዶ/ር) ከዛምቢያ ግብርና ሚኒስትር ሩበን ምቶሎ እና ከሞዛምቢክ የግብርና፣ አካባቢ እና አሳ ሃብት ሚኒስትር ሮቤርቶ ሚቶ አልቢኖ ጋር ባደረጉት ውይይት ኢትዮጵያ በግብርና ዘርፍ ማሻሻያዎችን በማድረግ ተጨባጭ ውጤት ማግኘቷን አብራርተዋል፡፡
እንዲሁም በንግድና ሌሎች ዘርፎች ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር እያከናወነች ያለውን ተግባር አስረድተዋል።
ኢትዮጵያ ቡናን ጨምሮ የተለያዩ የግብርና ምርቶችን ለውጭ ገበያ እያቀረበች መሆኗን በመግለጽ የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣናን በመጠቀም አህጉራዊ የንግድ ልውውጥን ማጠናከር እንደሚገባ አንስተዋል።
ከሁለቱ ሀገራት ጋር በተለያዩ የግብርና ዘርፎች በትብብር ሊሰሩባቸው የሚችሉ ጉዳዮች መኖራቸውን ጠቅሰው፥ የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ ትብብሮችን ለማጠናከር ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል።
የዛምቢያ ግብርና ሚኒስትር ሩበን ምቶሎ በበኩላቸው ሀገራቸው በግብርናው ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጋር መስራት እንደምትፈልግ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ በስንዴ፣ በሌማት ትሩፋት እና በሌሎች የግብርና ዘርፎች ካስመዘገበቻቸው ስኬቶች ልምድ መቅሰም እንደሚፈልጉም ጠቁመዋል።
ዛምቢያ ከኢትዮጵያ ጋር ስምምነት በመፈራረም በዘርፉ በጋራ መስራት እንደምትፈልግ ሚኒስትሩ አንስተዋል።
የሞዛምቢክ የግብርና፣ አካባቢና አሳ ሃብት ሚኒስትር ሮቤርቶ ሚቶ አልቢኖ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ጠንካራ የግብርና ሥርዓት በመገንባት ካስመዘገበችው ስኬት ትምህርት መውሰድ እንደሚፈልጉ ገልጸዋል።
በተለይም የስንዴ ምርትና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በተከናወኑ ተግባራት የተመዘገቡ ስኬቶች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን ነው ያነሱት።
ሆሳዕና ፤ ሚያዝያ 2/2018 (ኢዜአ)፦በሆሳእና፣ ወላይታ ሶዶና ቦንጋ ከተሞች በትንሳዔ በዓል ገበያ በቂ የምርትና የእርድ እንስሳት አቅርቦት መኖሩ ተመለከተ። ...
Apr 12, 2026
አዲስ አበባ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦የጉምሩክ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ የጉምሩክ አገልግሎት በሚያቀላጥፍ መልኩ እየተዘጋጀ መሆኑን በሕ...
Apr 9, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፦ የአፋር ሰመራ ሁለተኛ ደረጃ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ወደ ሥራ መግባቱ በክልሉ የሚገኘውን ሰፊ የእንስሳት ሀ...
Apr 1, 2026
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025