አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 22/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የግብርና ልማት ለበርካታ የአፍሪካ ሀገራት ምሳሌ እንደሚሆን የተለያዩ ሀገራት የግብርና ሚኒስትሮች ገለጹ።
በተለይም በስንዴ ምርት እያስመዘገበችው ያለው ስኬት የሚደነቅ መሆኑን አንስተዋል።
የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ(ዶ/ር) ከሁለተኛው የተመድ የምግብ ሥርዓት ጉባኤ በተጓዳኝ ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የግብርና ሚኒስትር እና ከካዛኪስታን ግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።
ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት ኢትዮጵያ ለግብርናው ዘርፍ የተለየ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች መሆኑንና በዚህም ተጨባጭ ውጤት መምጣቱን አብራርተዋል።
ለምርትና ምርታማነት መጨመር አስፈላጊ ግብዓቶችን በማሟላትና የግብርና ሜካናይዜሽንን ለማሳደግ የተለያዩ እርምጃዎች መወሰዳቸውንም አንስተዋል።
የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በሌማት ትሩፋትና በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብሮች የተጀመሩ ስራዎች የቤተሰብ የምግብ ፍጆታን ከማሟላት ባለፈ ትርፍ ምርት ለገበያ እየቀረበ እንደሚገኝ ነው ያብራሩት።
ኢትዮጵያ ለረጅም ዓመታት ስንዴን ከውጭ ታስገባ እንደነበር ያስታወሱት ሚኒስትሩ፣ በበጋና በክረምት በማምረት ከራሷ አልፋ ለውጭ ገበያ ማቅረብ ጀምራለች ብለዋል።
ምርትና ምርታማነትን የበለጠ ለማሳደግ የተሻለ ተሞክሮ ካላቸው ሀገራት ጋር የዕውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ማምጣት ላይ በጋራ እንደምትሰራ ጠቁመዋል።
የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የግብርናና ምግብ ደህንነት ሚኒስትር ግሪጎይር ካንጋጂ የኢትዮጵያ የግብርና ዕድገት ለበርካታ የአፍሪካ ሀገራት ተምሳሌት መሆኑን ገልጸዋል።
በተለይም በስንዴ ላይ ያሳየችውን ምርታማነት አድንቀው፣ ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ልምድ የመቅሰም ፍላጎት አላት ብለዋል።
በዚህም ከግብርና ሚኒስትሩ ጋር ተደጋጋሚ ውይይት ማድረጋቸውንና በቀጣይም ስትራቴጂክ አጋርነት መመስረት የሚያስችላቸውን ስምምነት እንደሚፈራረሙ አስታውቀዋል።
የካዛኪስታን ግብርና ምክትል ሚኒስትር የርቦል ታዙርኮቭ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በግብርና ልማት አስደናቂ የዕድገት ጉዞ ላይ እንደምትገኝ ገልጸዋል።
ካዛኪስታን ከኢትዮጵያ ጋር በግብርና በንግድ እና በኢንቨስትመንት ዘርፍ ያላትን ትብብር የበለጠ ማጠናከር እንደምትፈልግም ጠቁመዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025