
ሮቤ ፤ሐምሌ 22/2017 (ኢዜአ)፦በባሌ ዞን ከግብርና ወደ ኢንቨስትመንት ለተሸጋገሩ 98 አርሶ አደሮች እና ማህበራት የኢንቨስትመንት ፍቃድ ዛሬ መስጠቱን የዞኑ ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ጽህፈት ቤት ገለጸ።
የዞኑ ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መሐመድ ኢብሮ እንዳሉት በዞኑ ከግብርና ወደ ኢንቨስትመንት በመሸጋገር እውቅና ያገኙት 98 አርሶ አደሮች፣ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችና ማህበራት ናቸው።

አርሶ አደሮቹና ኢንተርፕራይዞቹ ባለፉት ዓመታት በተሰማሩበት የሥራ መስክ ውጤታማ ከመሆን ባሻገር ከ110 ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል ማስመዝገባቸውን ተናግረዋል።
ፕሮጀክቶቹ ወደ ሥራ ሲገቡ 3 ሺህ ለሚጠጉ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ እድል እንደሚፈጥሩም አክለዋል።
በዞኑ አርሶ አደሩ በመደበኛነት ከሚያመርተው ሰብል በተጓዳኝ የተለያዩ ኢኒሼቲቮችን ተግባራዊ በማድረግ ከግብርና ወደ ኢንቨስትመንት የሚሸጋገሩ አርሶ አደሮች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን የገለጹት ደግሞ በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ተወካይ አቶ ሙክታር ማሚያ ናቸው።
ከግብርና ወደ ኢንቨስትመንት የተሸጋገሩ አርሶ አደሮችና ማህበራት በሚሰማሩበት የስራ መስክ ውጤታማ እንዲሆኑ የመሬት አቅርቦትና ሌሎች የተለያዩ ማበረታቻዎች እንደሚደረግላቸውም አመልክተዋል።
ባለፉት ዓመታት በተሰማሩበት የሥራ መስክ ውጤታማ በመሆን ወደ ኢንቨስትመንት ከተሸጋገሩ አርሶ አደሮች መካከል አቶ ሬድዋን ሀጂ ማህሙድ፤ በግብርና ላይ በመሰማራት በሚያመርቱት ሰሊጥና ለውዝ ውጤታማ በመሆን እውቅና ማግኘታቸውን ተናግረዋል።
በአሁኑ ወቅት ወደ ኢንቨስትመንት በመሸጋገራቸው 10 ሄክታር መሬት በኢንቨስትመንት ማበረታቻነት ማግኘታቸውን ገልፀዋል።

በአካባቢው ከሚመረተው የስንዴ ምርት በተጨማሪ ገበያን ማዕከል በማድረግ የተለያዩ የገቢ ማስገኛ ኢኒሼቲቮችን ተግባራዊ በማድረግ ወደ ኢንቨስትመንት መሸጋገራቸውን የገለጹት ደግሞ ሌላው አርሶ አደር በሺር ሐጂ ኢስማኤል ናቸው።
በአሁኑ ወቅት በኢንቨስትመንት ማበረታቻነት የተሰጣቸው 10 ሄክታር መሬትና የእውቅና ሰርተፊኬት ይበልጥ ለተሻለ ሥራ እንዳነሳሳቸውም አክለዋል።
በባሌ ዞን ሽግግር ያደረጉትን ጨምሮ ከ2 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ 364 ባለሃብቶች በተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች መሰማራታቸውን ከዞኑ ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ጽህፈት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ሆሳዕና ፤ ሚያዝያ 2/2018 (ኢዜአ)፦በሆሳእና፣ ወላይታ ሶዶና ቦንጋ ከተሞች በትንሳዔ በዓል ገበያ በቂ የምርትና የእርድ እንስሳት አቅርቦት መኖሩ ተመለከተ። ...
Apr 12, 2026
አዲስ አበባ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦የጉምሩክ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ የጉምሩክ አገልግሎት በሚያቀላጥፍ መልኩ እየተዘጋጀ መሆኑን በሕ...
Apr 9, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፦ የአፋር ሰመራ ሁለተኛ ደረጃ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ወደ ሥራ መግባቱ በክልሉ የሚገኘውን ሰፊ የእንስሳት ሀ...
Apr 1, 2026
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025