
አዲስ አበባ፤ሐምሌ 22/2017 (ኢዜአ)፦በዓለም አቀፍ ደረጃ የምግብ ምርትን ለማሳደግ እና የዋጋ ንረትን ለማረጋጋት ሀገራት ትብብራቸውን የበለጠ ሊያጠናክሩ እንደሚገባ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ ገለጹ።
በአዲስ አበባ እየተካሄደ ካለው የዓለም የምግብ ሥርዓት ጉባኤ በተጓዳኝ እ.ኤ.አ የ2025 የዓለም የምግብ ዋስትናና የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት ሁኔታን የተመለከተ ሪፖርት ትናንት ምሽት ይፋ ሆኗል።

ሪፖርቱ የአየር ንብረት ለውጥና የተለያዩ ግጭቶች የዓለም የምግብ አቅርቦትና ዋጋ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደራቸውን አመላክቷል።
ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ በሪፖርቱ ይፋ ማድረጊያ መርሃግብር ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ በዓለም ላይ እየጨመረ የመጣው የምግብ እጥረትና የዋጋ መናር የሀገራት የጋራ መፍትሔ ያስፈልገዋል ብለዋል።
ችግሩ በተለይም አነስተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎችን የበለጠ የሚጎዳ መሆኑን ጠቅሰው፤ ቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ አዳጋች መሆኑን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን ለመቻል የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደች መሆኑን ያነሱት ፕሬዚዳንቱ፤ በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተጀመረው የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር ውጤታማ መሆኑን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ የምግብ ዋጋ መናርን ለመቀነስ እየተወሰዱ ባሉ እርምጃዎች ተጨባጭ ውጤቶች መገኘታቸውንም ነው የጠቀሱት።
በልማት ሴፍትኔት መርሃ ግብርም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ገልጸዋል።
በዓለም ላይ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦትን ለማረጋገጥ፣ ምርታማነትን ለመጨመር እና ሰላምን ለማፅናት ሀገራት በጋራ ሊሠሩ እንደሚገባ ነው ያመለከቱት።

የተመድ ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና መሀመድ በበኩላቸው፤ የምግብ ዋጋ እየጨመረ መምጣት በርካታ የዓለም ዜጎች የምግብ ዋስትናቸው እንዳይረጋገጥ ማድረጉን ነው ያነሱት።
የአየር ንብረት ለውጥና የተለያዩ ግጭቶች የዓለም የምግብ አቅርቦትና ዋጋ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደራቸውንም አንስተዋል።
በዓለም በርካታ ህፃናት በምግብ እጥረት ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው መቅረታቸውንም ነው ያነሱት።
በዓለም ላይ ግጭትን ማስቀረት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው፣ ለዚህ ደግሞ የጋራ ትብብርና ተግባራዊ እርምጃ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴድሮስ አድሃኖም (ዶ/ር) በበበይነ መረብ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት፤ የተፈጥሮ አደጋዎችና ግጭት ለጤና አስፈላጊ ምግቦች አቅርቦት ላይ እጥረት ፈጥሯል።
ይህ የምግብ ሥርዓት መዛባት በርካታ ዜጎችን ለጤና እክል ተጋላጭ ማድረጉንም አንስተዋል።
የዓለም መንግስታት የሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች በምግብ ሥርዓት ላይ እያደረሰ ያለውን አሉታዊ ተጽዕኖ ለመከላከል የበለጠ ትብብራቸውን ሊያጠናክሩ እንደሚገባም አመልክተዋል።
ሆሳዕና ፤ ሚያዝያ 2/2018 (ኢዜአ)፦በሆሳእና፣ ወላይታ ሶዶና ቦንጋ ከተሞች በትንሳዔ በዓል ገበያ በቂ የምርትና የእርድ እንስሳት አቅርቦት መኖሩ ተመለከተ። ...
Apr 12, 2026
አዲስ አበባ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦የጉምሩክ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ የጉምሩክ አገልግሎት በሚያቀላጥፍ መልኩ እየተዘጋጀ መሆኑን በሕ...
Apr 9, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፦ የአፋር ሰመራ ሁለተኛ ደረጃ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ወደ ሥራ መግባቱ በክልሉ የሚገኘውን ሰፊ የእንስሳት ሀ...
Apr 1, 2026
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025