
አዲስ አበባ፤ሐምሌ 22/2017 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በግብርና፣ ንግድ እና ኢንቨስትመንት ዘርፍ ያሉ አማራጮችን በመጠቀም ግንኙነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰሩ ገለጹ።
ከሁለተኛ የምግብ ስርዓት ጉባኤ ጎን ለጎን የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ(ዶ/ር) ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የአካባቢና አየር ንብረት ለውጥ ሚኒስትር አምና አልደሃክ (ዶ/ር) ጋር ውይይት አድርገዋል።
ሚኒስትሮቹ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ጠንካራና ስትራቴጂካዊ ግንኙነት በውይይታቸው አንስተዋል።
የኢፌዲሪ ግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ(ዶ/ር) ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ ያላትን አቅምና እያከናወነች ያለውን ተግባር አብራርተዋል።
ኢትዮጵያ ቡናና የእንስሳት ውጤቶችን ወደ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እንደምትልክ ገልጸው፤ ይህንን ግንኙነት የበለጠ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።
ኢትዮጵያ በግብርና ኢንቨስትመንት ዘርፍ በርካታ አማራጮች እንዳላት በመጥቀስ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ባለሃብቶች በግብርና ማቀነባበሪያ፣ማዳበሪያ ፋብሪካና ሌሎች ዘርፎች መሰማራት የሚችሉባቸው አማራጮች እንደሆኑ አብራርተውላቸዋል።
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የአካባቢና አየር ንብረት ለውጥ ሚኒስትር አምና አልደሃክ (ዶ/ር) በበኩላቸው፥ ከኢትዮጵያ ጋር በንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፍ በትብብር መስራት እንደሚፈልጉ ገልጸውዋል።
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ባለሃብቶች በግብርና ኢንቨስትመንት ዘርፎች የመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል።
ሚኒስትሮች በሁለቱ አገራት መካከል በግብርና፤ንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፍ ያሉ አማራጮችን ለመጠቀም ያለውን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ለመስራት ተስማምተዋል።
ሆሳዕና ፤ ሚያዝያ 2/2018 (ኢዜአ)፦በሆሳእና፣ ወላይታ ሶዶና ቦንጋ ከተሞች በትንሳዔ በዓል ገበያ በቂ የምርትና የእርድ እንስሳት አቅርቦት መኖሩ ተመለከተ። ...
Apr 12, 2026
አዲስ አበባ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦የጉምሩክ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ የጉምሩክ አገልግሎት በሚያቀላጥፍ መልኩ እየተዘጋጀ መሆኑን በሕ...
Apr 9, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፦ የአፋር ሰመራ ሁለተኛ ደረጃ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ወደ ሥራ መግባቱ በክልሉ የሚገኘውን ሰፊ የእንስሳት ሀ...
Apr 1, 2026
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025