አዳማ፤ ሐምሌ 22/2017(ኢዜአ)፡- በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ ለመሰብሰብ እየተደረገ ባለው እንቅስቃሴ የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ገቢዎች ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
በበጀት ዓመቱ ከደረሰኝ አቆራረጥ ጋር ተያይዞ የተጠናከረ ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ ጥፋተኛ ሆነው የተገኙ 82 ነጋዴዎች ላይ 7 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር ቅጣት እንደተጣለባቸውና ህጋዊ እርምጃ እንደተወሰደባቸውም ጽህፈት ቤቱ አስታውቀዋል።
በ2017 በጀት ዓመት በዞኑ ከመዘጋጃ ቤታዊ፣ ከቀጥታ ታክስ እና ቀጥታ ካልሆነ ታክስ 4 ነጥብ 17 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ ከእቅድ በላይ ማሳካት መቻሉም ተመላክቷል።
የምስራቅ ሸዋ ዞን ገቢዎች ጽህፈት ቤቱ ኃላፊ ወይዘሮ በድሪያ ረሽድ ለኢዜአ እንደገለጹት ጽህፈት ቤቱ ለዞኑ ህዝብ ሁለንተናዊ የልማት ተጠቃሚነት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል ገቢ ለመሰብሰብ ሲሰራ ቆይቷል።
በተለይም ባለፉት የለውጥ ዓመታት የዞኑን ገቢ ለማሳደግ በተደረገው ጥረት የሚሰበሰበው ገቢ መሻሻል ማሳየቱን አመላክተዋል።
በዚህ ረገድ የዞኑ ኢኮኖሚ ከሚያመነጨው ሀብት አኳያ የተሻለ ገቢ ለመሰብሰብ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ምቹና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን ነው የሚናገሩት።
በ2017 በጀት ዓመት ከማዘጋጃ ቤታዊ፣ ከታክስ ኦዲት፣ ከቀጥታ ታክስ እና ቀጥታ ካልሆነ ታክስ 4 ነጥብ 17 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ ከእቅድ በላይ 4 ነጥብ 25 ቢሊዮን ብር ገቢ ማሳካት ተችሏል ብለዋል።
መቂና መተሐራ ከተሞችን ጨምሮ ከ11 ወረዳዎች የተሰበሰበው የገቢ አፈጸፃጸም ካለፉት ዓመታት ከነበረው ገቢ ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ለውጥና መሻሻል የታየበት መሆኑንም አመላክተዋል።
ለገቢው ማደግ አስተዋጽኦ ካደረጉት መካከል የገቢ አሰባሰብ አሠራሩን በማዘመን ግብር ከፋዮች ከሰው ንክኪና ብልሹ አሠራር በፀዳ መልኩ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል ዘመናዊ የኢ-ታክስ አገልግሎት ተግባራዊ መደረጉ ተጠቃሽ መሆኑን አስረደተዋል።
እንዲሁም የግብር ሥርዓት ውስጥ ያልገቡትን በሕጉ መሠረት ወደ ግብር ሥርዓቱ እንዲገቡ በማድረግና ወቅቱን ያላገናዘብ ግብር የሚከፍሉትም ወቅታዊ እንዲሆኑ መደረጉ ለገቢው ማደግና ውጤት መገኘት አስተዋጽኦ ማድረጉን አውስተዋል።
በተለይም የንግዱ ማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማጎልበት፤ የሕግ ማስከበር ሥራ በተጠናከረ ሁኔታ መሠራቱ፣ በየደረጃው የአገልጋይነት ስሜት እንዲጎለብት አሠራርን በማሻሻልና በማዘመን በገቢ አሰባሰብ ሥርዓቱ ላይ አዎንታዊ ተፅዕኖ ማሳደር መቻሉን አብራርተዋል፡፡
ለግብር ከፋዮች የተፈጠረው ምቹና የተሳለጠ የክፍያ ሥርዓት የገቢ አቅምን አሳድጓል ያሉት ኃላፊዋ በአሁኑ ወቅት በዞኑ ደረጃ “ሀ” ፣ “ለ” እና “ሐ” 12 ሺህ 617 ግብር ከፋዮች እንደሚገኙ አስታውቀዋል።
በቀጣይም የአገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻልና በቴክኖሎጂ መደገፍ፣ የታክስ ማሳወቅና የታክስ ኦዲት ስራዎችን ማጠናከር የገቢ አቅምን ለማጎልበት የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።
በበጀት ዓመቱ ከደረሰኝ አቆራረጥ ጋር ተያይዞ የተጠናከረ ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ ጥፋተኛ ሆነው የተገኙ 82 ነጋዴዎች ላይ 7 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር ቅጣት እንደተጣለባቸውና ህጋዊ እርምጃ እንደተወሰደባቸው ገልፀዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025