አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 21/2017(ኢዜአ)፦በቀጣናው የምግብ ስርዓትን በማጠናከር የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በአህጉራዊ ማዕቀፍ በጋራ እንደሚሰሩ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን /ኢጋድ/ አባል ሀገራት አስታወቁ፡፡
የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ያሉ ቀጣናዊ ዕድሎችን በተመለከተ በአዲስ አበባ ሲካሄድ የነበረው የኢጋድ አባል ሀገራት ባለሙያዎች ስብሰባ በትናትናው ዕለት መጠናቀቁ ይታወቃል፡፡
ስብሰባው በግብርናው ዘርፍ አንገብጋቢ የሆኑ ችግሮችን በመለየት ለመፍታትና ለ2ኛው የተመድ የምግብ ሥርዓት ጉባኤ ለማዘጋጀት ያለመ ነው፡፡
ይሄንን ተከትሎ የኢጋድ ዋና ጸሀፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ን ጨምሮ የአባል ሀገራቱ ሚኒስትሮች በተገኙበት የተደረገው ስብሰባ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል፡፡
በኢጋድ ቀጣና የስርዓተ ምግብ ሽግግር በማሳለጥ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥና ረሃብን መከላከል የሚያስችል አህጉራዊ የቅንጅት ማዕቀፍ እንደሚፈጥሩ አረጋግጠዋል፡፡
ቴክኖሎጂዎችና የተሻሻሉ የምርጥ ዘር ዝርያዎችን በመጠቀም እንዲሁም የስርዓተ ምህዳር ብዝሃነትን በማስፋፋት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በትብብር እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡
ዘላቂ የመሬትና ውሃ አጠቃቀምን በማስፋት ስነ ምህዳርን የመቋቋም አቅም ያላቸው ዝርያዎችን ማስፋት በትኩረት ይሰራበታልም ተብሏል፡፡
የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦትን ለማሻሻል ቀጣናዊ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዓትን ማጠናከር፣ የአደጋ ጊዜ እቅድ ማውጣትና እንደ በረሀ አንበጣ ያሉ ተባዮች እና የእንስሳት በሽታዎችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በትብብር እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል፡፡
የአየር ንብረት ለውጥ ለመከላከልና የልማት የፋይናንስ አማራጮችን ያካተተ አዳዲስ የፋይናንስ ሥልት እንዲዳብር ይደረጋል ተብሏል፡፡
ተቋማዊ አቅምን፣ የፋይናንስ ስርዓቱን፣ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ መሰረተ ልማትን ከቀጣናዊ ፖሊሲዎች ጋር በማጣጣም ምቹ አሰራር እንደሚፈጠር ተገልጿል፡፡
በኢጋድ አስተባባሪነት የተቀናጀ ቀጣናዊ የቴክኒክ ግብረ ኃይል እንዲቋቋም እንደሚደግፉም ተጠቁሟል፡፡
የአባል ሀገራቱን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በኢጋድ ዋና ጸሀፊ አስተባባሪነት የጋራ ፕሮግራሞች ተቀርጸው ውይይቶች ይዘጋጃሉ ተብሏል፡፡
በኢጋድ እና በአጋሮቹ አመቻችነት የቀጣይ የቴክኒክ ኮሚቴው ስብሰባ በስድስት ወራት ውስጥ እንዲጠራ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025