ወልቂጤ፤ሐምሌ 17/2017(ኢዜአ)፦በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከቱሪዝም ዘርፍ ከ1 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ገለፁ።
ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ ምክር ቤት የክልሉን መንግስት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ሲያቀርቡ እንዳመለከቱት፥ የክልሉን የገቢ አቅም የማሳደግና ያሉትን አማራጮች አሟጦ ለመጠቀም የተደረጉ ጥረቶች ውጤታማ ናቸው።
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የክልሉን ኢኮኖሚ ለማሳደግ ያሉ አቅሞችን ለይቶ ወደስራ በመገባቱና ትኩረት ተሰጥቶ በመሰራቱ ውጤት መገኘቱን ተናግረዋል።
በተለይም በቱሪዝም ዘርፍ በክልሉ ያሉ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ የቱሪስት መስህቦችን በማልማትና በማስተዋወቅ ገቢን ለማጠናከር ግብ ተይዞ ወደ ሥራ መገባቱን አስታውሰዋል።
በዚህም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 13 ሺህ 698 የውጭ ሃገር ቱሪስቶች እና 755 ሺህ 689 የሀገር ውስጥ ቱሪስቶች ክልሉን እንደጎበኙ የተናገሩት እንዳሻው (ዶ/ር)፣በዚህም ከ1 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተገኝቷል ብለዋል።
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከተለያዩ የገቢ አርዕስቶች 16 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ገቢ ቢሰበሰብም የክልሉ ኢኮኖሚ ከሚያመነጨው አንጻር የበለጠ ገቢ መሰብሰብ የሚያስችል ዕድል አለ።
ያለ ደረሰኝ የሚደረግ ግብይት፣ የግብር ስወራና ለዚህ ተባባሪ የሚሆኑ የዘርፉ አካላት ችግር እየፈጠሩ መሆኑን ገልጸው፣ ችግሩን ለመፍታት የግንዛቤና የህግ ማስከበር ሥራ መሰራቱን ተናግረዋል።
በተደረገ ፍተሻ ያለደረሰኝ ግብይት ሲፈጽሙና በሌሎች ተገቢ ባልሆነ ተግባር ላይ ተሰማርተው በተገኙ 784 ግብር ከፋዮች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዷል ብለዋል።
በዚህም ተሰውሮ የነበረ 99 ሚሊዮን የታክስ ግኝትን ለማስመለስ ተችሏል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ ለችግሩ ምክንያት ናቸው በተባሉ 164 ፈጻሚዎች ላይም አስተዳደራዊና ህጋዊ እርምጃ መወሰዱን ጠቁመዋል።
በክልሉ 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ''በአንድ ከተማ አንድ ፕሮጀክት ኢኒሼቲቭ" በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑንም አስታውሰዋል።
የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄን መነሻ በማድረግ በክልሉ አስር መዋቅሮች ሞዴል የህዝብ መጸዳጃ ቤቶች ግንባታ ወደ ተግባር መገባቱንም ርዕሰ መስተዳድሩ በሪፖርታቸው አመላክተዋል።
ለዚህም ከህብረተሰቡ ከ623 ሚሊዮን 274 ሺህ በላይ ሀብት ለማሰባሰብ መቻሉን ተናግረዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025