አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 17/2017(ኢዜአ)፦ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ተግባራት ስኬት እንዲያስመዘግቡ የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር ሊጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ።
ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ እያከናወነች ያለውን ተግባራት በተመለከተ ኢዜአ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ቆይታ አድርጓል።
ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናዋን ለማረጋገጥ ስንዴን ጨምሮ የተለያዩ ምግቦችን እስከ ቅርብ ጊዜ ከውጭ ታስገባ እንደነበር አይዘነጋም።
መንግስት ህዝቡን በማስተባበር የጀመራቸው ሥራዎች ምግብን ከጓሮ ከማምረት ባለፈ ለሰው ልጅ የአካልና አዕምሮ አስፈላጊ ንጥረ ነገሮችን የያዙ ምግቦችን የመመገብ ልምምድ እየጎለበተ መጥቷል።
ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ኢትዮጵያ በምግብ ራስን ለመቻል እያከናወነችው ያለው ተግባራት ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢኒስቲትዩት ሥርዓተ-ምግብ ሽግግር የክልሎች አስተባባሪ አካሉ ደፊሳ እንደሚናገሩት፤ የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ከሀገር ደህንነት ተለይቶ ሊታይ አይገባም።
ቀደም ባሉት ዓመታት አንድ ሀገር የምግብ ዋስትናውን በማምረትም በመግዛትም ሊያረጋግጥ እንደሚችል ጠቅሰው፤ አሁን ካለው የዓለም ነባራዊ ሁኔታ አኳያ ግን ይህን ማድረግ አስቸጋሪ መሆኑን አመላክተዋል።
ለአብነትም በኮቪድ ጊዜ ምግባቸውን የማያመርቱ ሀገራት በሚፈልጉት ጊዜ ምግብ መግዛት አለመቻላቸውን አስታውሰዋል።
ምርትና ምርታማነትን አሳድጎ ለዜጎቹ በቂ ምግብ ማቅረብ የሚችል ሀገር ከራሱ አልፎ ለሌሎች መትረፍና የሀገሩን ብሄራዊ ደህንነት ማስጠበቅ የሚችል ነው ብለዋል።
የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አለማየሁ ወጫቶ(ዶ/ር)፤ ከሀገራዊ ለውጡ በኋላ የተረጂነት አስተሳሰብን ለመቀየር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን ጨምሮ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ሰፊ ርብርብ ተደርጓል ይላሉ።
በዚህም ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም መሸፈን የሚያስችሉ ተግባራዊ እንቅስቃሴ መጀመሩንና በርካታ ዜጎችንም ከተረጂነት አስተሳሰብ ማውጣት መቻሉን አብራርተዋል።
በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የሥነ-ምግብ መምህርት ዘላለም ሲሳይ በበኩላቸው፤ ጤናማ አመጋገብ ያለው ማህበረሰብ አዳዲስ ነገሮችን የመፍጠር አቅም እንዳለው ጠቅሰው፤ በአካልና በአዕምሮ የዳበረ ዜጋ ለማፍራት ሥርዓተ-ምግብ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል።
ምርትና ምርታማነትን ከማሳደግ ባለፈ ፍትሃዊ የምግብ ሥርጭትን ማረጋገጥ እንደሚገባ የስነ-ምግብ መምህርቷ ይናገራሉ።
በጤና ሚኒስቴር የሰቆጣ ቃልኪዳን ምክትል አስተባባሪ ፍስሃ ተክሌ በኢትዮጵያ ከሁለት ዓመት በታች የሆኑ ህፃናት በተመጣጠነ ምግብ እጥረት ለመቀንጨር ችግር ተጋላጭ መሆናቸውን አንስተዋል።
ይህን ችግር ለመከላከል የሰቆጣ ስምምነት መፈረሙንና በዚህም የጨቅላ ህፃናትን ሞትና የመቀንጨር ምጣኔን መቀነስ መቻሉን ተናግረዋል።
በጤና ሚኒስቴር የሰቆጣ ቃልኪዳን ምክትል አስተባባሪ ፍስሃ ተክሌ ቀደም ባሉት ዓመታት በአንዳንድ ክልሎች የመቀንጨር ችግር በስፋት ማጋጠሙንም ገልጸዋል።
ከሰቆጣ የቃልኪዳን ስምምነት በኋላ የህፃናትን መቀንጨርና ሞት በከፍተኛ ሁኔታ የቀነሱ ስራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አለማየሁ ወጫቶ(ዶ/ር) ከዕለት ደራሽ ባለፈ እያንዳንዱ ክልል ከሚያመርተው ላይ የመጠባበቂያ ምግብ ክምችት እንዲይዝ ተደርጓል ብለዋል።
ኢትዮጵያ የሥርዓተ-ምግብ ሽግግርን ለማፋጠን የተለያዩ ኢኒሼቲቮችን ቀርፃ ተግባራዊ እያደረገች ነው።
ከእነዚህም መካከል ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ፣ አረንጓዴ ዐሻራ፣ የሌማት ትሩፋትና የከተማ ግብርና ተጠቃሽ ናቸው።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025