አዲስ አበባ፤ሐምሌ 16/2017 (ኢዜአ):-ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም ግብርናን ለመተግበር በትኩረት እየሰራች መሆኑን የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ገለጸ።
በአፍሪካ የምግብ ስርዓት ላይ ያተኮረ የአፍሪካ ሼፎች ስብሰባ እና የፖሊሲ ጉባዔ እየተካሄደ ነው።
''ምግቤ አፍሪካዊ ነው''በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ በሚገኘው ጉባዔ ከተለያዩ የአፍሪካ አገራት የመጡ ሼፎች እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ሀላፊዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
የፕላንና ልማት ሚኒስትር አማካሪ ሀና አበበ በወቅቱ እንደገለጹት፥ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል እና ስነ-ምህዳሮቿን ለመጠበቅ በቁርጠኝነት እየሰራች ነው።
በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አማካኝነት በደን መልሶ ልማት እና የተራቆቱ መሬቶችን ወደ ነበሩበት ለመመለስ የተሰራውን ውጤታማ ስራንም ለአብነት ጠቅሰዋል።
ኢትዮጵያ የምግብ ስርዓትን ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ለማጣጣም የሚያስችሉ የፖሊሲ እርምጃዎች መውሰዷን አስታውቀዋል፡፡
ፖሊሲው የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም ግብርና ላይ ኢንቨስት ማድረግ፣ የተራቆቱ መሬቶችን ወደ ለምነት መመለስ፣አርሶ አደሮችን በተለይም ሴቶችን እና ወጣቶችን ማብቃት እንዲሁም ዘላቂ ፍጆታን ማበረታታት ላይ ማተኮሯን አብራርተዋል።
በተጨማሪም ኢትዮጵያ ከአፍሪካ የምግብ ሉዓላዊነት ጥምረት ጋር በተለያዩ ደረጃዎች በተጠናከረ ሁኔታ እየሰራች እንደምትገኝ አመልክተዋል።
ጉባኤው መንግስት እና የሲቪል ማህበረሰቡ አባላት በአህጉሪቱ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በጋራ እንዲሰሩ ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥር ተናግረዋል።
የአፍሪካ የምግብ ሉዓላዊነት ጥምረት የቦርድ አባል ፋሲል ገበየው (ዶ/ር) በበኩላቸው፥ ፍትሃዊና ዘላቂ የአፍሪካ የምግብ ስርዓት ለመፍጠር በትብብር መስራት እንደሚገባ ነው የገለጹት፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025