
አዲስ አበባ፤ሐምሌ 15/2017(ኢዜአ)፦የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው የውጭ ምንዛሪ ክምችትና አቅርቦትን በማሳደግ የተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚ መፍጠር ማስቻሉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ ገለጹ፡፡
የግሉን ዘርፍ ተዋናዮችን፣ ፖሊሲ አውጪዎችንና የፋይናንስ ተቋማትን በማሳተፍ በዘላቂ ልማት፣ በማክሮ ኢኮኖሚ፣ በመዋቅራዊና በንግድ ዙሪያ የሚመክር የኢትዮጵያ የፋይናንስ ጉባኤ የግል ዘርፍ መድረክ ተካሂዷል፡፡

የፕላንና ልማት ሚኒስቴር፣ የገንዘብ ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በትብብር ባዘጋጁት በዚህ ጉባኤ የማክሮ ኢኮኖሚ መዋቅራዊ ማሻሻያ፣ የፋይናንስ ዘርፍ ሪፎርምና የኢንቨስትመንት ዕድሎች፣ ለአካታች ፋይናንስና ልማት የብድር አገልግሎት ማመቻቸት፣ የኢንቨስትመንት ከባቢ በኢትዮጵያ እና የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ የታሪክና የእምቅ የተፈጥሮ ሀብት ባለቤት ብትሆንም በጸጋዋ ልክ መልማት አልቻለችም፡፡
ከልመና ያለወጣ ሀገር ነፃነት የለውም ያሉት የባንኩ ገዥ ችግሮችን ተጋፍጦ የዜጎችን ድህንነትና የሀገርን ብልጽግና ማረጋገጥ የሁሉም ተቀዳሚ ተግባር ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡
የተረጋጋ የማክሮ ኢኮኖሚ እና ቀጣይነት ያለው የሀገር ዕድገትን ለማረጋገጥ የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲ ገቢራዊ መደረጉንም ገልጸዋል፡፡
በዚህም የዋጋ ግሽበትን በግማሽ መቀነስ፣ የውጭ ምንዛሪ በገበያ እንዲወሰን በማድረግ የምንዛሪ ክምችትን ማሳደግ እንዲሁም በመሰረታዊ ዘርፎች ላይ ምርታማነትን መጨመር ተችሏል ብለዋል፡፡
የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያውም አስደናቂ ውጤት ማምጣቱን ጠቅሰው፤ ዘመናዊና ለልማት የሚመች የፋይናንስ ዘርፍ እንዲኖር ምቹ ሁኔታ እየፈጠረ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
መንግስት በ2016 በጀት ዓመት ከሁሉም ምንጮች ያገኘው የውጭ ምንዛሪ ግኝት 24 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር እንደነበር አስታወሰው፣ ከተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ወዲህ በ2017 በጀት ዓመት 32 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር መገኘቱን ገልጸዋል፡፡
የሀገር እድገት በመንግስት ብቻ የሚረጋገጥ አይደለም ያሉት የባንኩ ገዥ፤ የግሉ ዘርፍ የነቃ ተሳትፎና ትብብር ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።
የዛሬው ጉባኤም የግሉ ዘርፍ በመንግሥት ፖሊሲዎች ላይ ግልጽነት በመፍጠር በሁሉም ዘርፎች የተመዘገቡ ውጤቶችን ለማስቀጠል ምክክር የሚደረግበት መሆኑን ገልጸዋል።
ሆሳዕና ፤ ሚያዝያ 2/2018 (ኢዜአ)፦በሆሳእና፣ ወላይታ ሶዶና ቦንጋ ከተሞች በትንሳዔ በዓል ገበያ በቂ የምርትና የእርድ እንስሳት አቅርቦት መኖሩ ተመለከተ። ...
Apr 12, 2026
አዲስ አበባ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦የጉምሩክ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ የጉምሩክ አገልግሎት በሚያቀላጥፍ መልኩ እየተዘጋጀ መሆኑን በሕ...
Apr 9, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፦ የአፋር ሰመራ ሁለተኛ ደረጃ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ወደ ሥራ መግባቱ በክልሉ የሚገኘውን ሰፊ የእንስሳት ሀ...
Apr 1, 2026
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025