ሰቆጣ ፤ ሐምሌ 15/2017(ኢዜአ)፡- በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ለ2017/2018 የምርት ዘመን 230 ሺህ 909 ሜትር ኪዩብ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ተዘጋጅቶ ጥቅም ላይ መዋሉን የብሔረሰብ አስተዳደሩ ግብርና መምሪያ አስታወቀ።
የተፈጥሮ ማዳበሪያ ወጪን ከመቀነስ ባለፈ ይህንኑ ግብአት ተጠቅመው የእርሻ ስራቸውን በወቅቱ ለማከናወን ይበልጥ እንደጠቀማቸው በአስተዳደሩ የሰቆጣ ወረዳ አርሶ አደሮች ገልጸዋል።
የብሔረሰብ አስተዳደሩ ግብርና መምሪያ ሃላፊ አቶ አዲስ ወልዴ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ በ2017/2018 የምርት ዘመን 230 ሺህ 909 ሜትር ኪዩብ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ተዘጋጅቶ ጥቅም ላይ ውሏል።
የአርሶ አደሩ የተፈጥሮ ማዳበሪያ የማዘጋጀት ልምድ እያደገ መምጣቱን ጠቅሰው፤ በዚህም የሰብል ምርታማነታቸውን ይበልጥ ለማሳደግ የተጠናከረ የባለሙያዎች ድጋፍና ክትትል እየተደረገ ነው ብለዋል።
አርሶ አደሩ የተፈጥሮ ማዳበሪያን ጥቅም ላይ ከማዋልም ባለፈ እርጥበትን ማቀብ የሚያስችሉ አነስተኛ ጉድጓዶች በማሳ ላይ እየተደረገ መሆኑን አንስተዋል።
በሰቆጣ ዙሪያ ወረዳ ኢዜአ ያነጋገራቸው የሳይዳ ቀበሌ አርሶ አደር ይመር አበበ በሰጡት አስተያየት፤ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ቀጣይነት ያለው ምርታማነትን ለማሳደግ አጋዥ እንደሆናቸው ተናግረዋል።
በየዓመቱ የተፈጥሮ ማዳበሪያ እያዘጋጁ ተጠቃሚ እንደሆኑና ወጪም እንደቀነሰላቸው አውስተው፤ ለዘንድሮው የመኽር እርሻ በግብአትነት የሚውል ሶስት ሜትር ስፋት በሁለት ሜትር ጥልቀት ያለው ጉድጓድ በባለሙያ ታግዘው በመቆፈር የተፈጥሮ ማዳበሪያ ማዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።
በበጋ ወራት ያዘጋጁትን ማዳበሪያም በግማሽ ሄክታር የእርሻ መሬታቸው ላይ ጥቅም ላይ አውለው ስንዴ መዝራታቸውን አርሶ አደር ይመር ተናግረዋል።
ሌላው አርሶ አደር ገብረየስ በለጠ በበኩላቸው፤ 60 ኩንታል የተፈጥሮ ማዳበሪያ በፍግ አዘጋጅተው በእርሻ ማሳቸው ላይ በመበተን ጥቅም ላይ እንዳዋሉ ገልጸዋል።
የተፈጥሮ አፈር ማዳበሪያ መጠቀም መቻላችን ዘላቂ የሆነ የአፈር ለምነትን ጠብቆ ያቆይልናል ያሉት አርሶ አደር ገብረየስ፤ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ወጪን ከመቀነስ ባለፈ የእርሻ ስራቸውን በወቅቱ ለማከናወን ይበልጥ እንደጠቀማቸው አስረድተዋል።
በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በምርት ዘመኑ 120 ሺህ 638 ሄክታር መሬት በተለያየ የሰብል ዘር ለማልማት ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ከግብርና መምሪያው የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025