የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በመዲናዋ የሥራ ዕድል ፈጠራና ገበያን የማረጋጋት ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ -ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Jul 22, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ሐምሌ14/2017(ኢዜአ)፡-በአዲስ አበባ ከተማ የሥራ ዕድል ፈጠራና ገበያን የማረጋጋት ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም ግምገማና የ2018 በጀት ዓመት እቅድ ውይይት ተካሂዷል።


ከንቲባ አዳነች አቤቤ በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ የ2018 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎችን አመላክተዋል።

በአዲስ አበባ በ2017 በጀት ዓመት በመሰረተ ልማት አቅርቦት፣ በሰው ተኮር ሥራዎች፣ በበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች፣ በኮሪደር ልማትና በሌሎች መስኮችም የዜጎችን ተጠቃሚነት ያሳደጉ ተግባራት መከናወናቸውን ተናግረዋል።

በዚህም በኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ዘርፎች ስኬታማ ተግባራት መከናወናቸውን ነው ያብራሩት።


በአዲሱ በጀት ዓመትም በትኩረት ከሚከናወኑ ተግባራት መካከል የሥራ እድል ፈጠራ አንዱ መሆኑን ገልጸው፤ በዚህም 350 ሺህ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል ለመፍጠር እቅድ መያዙን ተናግረዋል።

ለሥራ ዕድል ፈጠራ ያሉ አቅሞችን መለየትና ለውጤታማነቱ መትጋት እንደሚጠበቅ አመልክተዋል።

የኑሮ ውድነት ጫናን ለመቀነስ ገበያን የሚያረጋጉ ተግባራት በቀጣይ ትኩረት የተሰጣቸው መሆኑን ያነሱት ከንቲባዋ፤ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ሌላው የርብርብ ማዕከል ነው ብለዋል።

የገበያ ማእከላትን ማስፋፋትና በአግባቡ አገልግሎት እንዲሰጡ ከማድረግ ባለፈ አምራች ኢንዱስትሪዎች ተኪ ምርቶችን በስፋት እንዲያመርቱ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።

የከተማው ኢኮኖሚ የሚያመነጨውን ገቢ በሚፈለገው መጠን ለመሰብሰብም የቴክኖሎጂዎች አጠቃቀምን ማጎልበትና ተያያዥ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መቀነስ ሌላው ትኩረት መሆኑንም አስረድተዋል።

ከመሰረተ ልማት አቅርቦት አኳያም የውኃ፣ የኤሌክትሪክ፣ የትራንስፖርት አገልግሎቶችን ማጎልበት ላይ ትኩረት እንደሚደረግና ያልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች ለማጠናቀቅ ርብርብ ይደረጋል ብለዋል።

በከተማ አስተዳደሩ ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶችን የተሻለ ለማድረግ የሪፎርም ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

አዲስ መሶብ የተሰኘውን የአንድ ማዕከል አገልግሎት ለማስጀመር በሂደት ላይ መሆናቸውን ገልጸው፤ ይህም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት በሚደረገው ጥረት አዎንታዊ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አመልክተዋል።

በከተማዋ የቱሪስት ፍሰቱን ለማሳደግ እንደሚሰራ ጠቁመው የሴቶች፣ ወጣቶችና አካል ጉዳተኞችን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ አካታች አሰራሮች ቀጣይነት ባለው መልኩ እንደሚተገበሩ አብራርተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጃንጥራር አባይ በበኩላቸው የተገኙ ውጤቶችን በማስቀጠል ለላቀ ውጤት መትጋት እንደሚገባ ገልጸዋል።


የኀብረተሰቡን እርካታ ለመጨመር የተያዙ ግቦች እንዲሳኩ አመራሩ በቁርጠኝነት መሥራቱን ይበልጥ ሊያጠናክር እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል።

በብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሞገስ ባልቻ እንደገለጹት፤ አሰባሳቢ ትርክት ግንባታ ለማሳካት የአመራሩ ሚና ጉልህ መሆኑን በመያዝ መስራት ይገባል ነው ያሉት።


በመዲናዋ የተሰሩ ሜጋ ፕሮጀክቶችን ለትርክት ግንባታ መጠቀም እንደሚገባ ገልጸው የድህረ እውነት ፈተናዎችን በመታገል ውጤት ለማምጣት አመራሩ ከመቼውም ጊዜ በላይ ዝግጁ ሊሆን እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ተቋማት ራሳቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ ይገባል- ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...

Feb 28, 2025

<p>በክልሉ የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች እየተከናወኑ ነው</p>

ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...

Feb 28, 2025

<p>ተቋማቱ በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...

Feb 28, 2025

<p>በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን ለማጠናቅ እየተሰራ ነው</p>

ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...

Feb 24, 2025