ሐረር፤ ሐምሌ 2/2017(ኢዜአ)፦ የሐረር ከተማ የኮሪደር ልማት ስራዎች ቃል በተግባር የተገለጸባቸው ናቸው ሲሉ በብልፅግና ፓርቲ የዋናው ጽህፈት ቤት የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ መለስ አለሙ ገለጹ።
አቶ መለስ አለሙን ጨምሮ የፓርቲው የወጣቶችና ሴቶች ክንፍ እና ሌሎች አመራሮች በሐረር ከተማ የተከናወኑ የኮሪደርና ሌሎች የልማት ስራዎችት ተመልክተዋል።
በወቅቱም አቶ መለስ አለሙ እንደገለጹት በከተማው የተከናወኑ የኮሪደር ልማት ስራዎች ቃል በተግባር የተገለጸባቸው ናቸው።
በአንድ ዓመት ውስጥ የተከናወኑ የኮሪደር እና ሌሎች የልማት ስራዎች ለሰው ልጅ ምቹ ሆነው የተሰሩና ሀገሪቱም ትልቅ ተስፋ ሰንቃ እየሰራች መሆኑን የሚያሳዩ ናቸው ብለዋል።
አመራሩና ህዝቡ ከተሞቻቸውን ለማልማት በቁርጠኝነት እየሰሩና አዲስ ምዕራፍ መክፈታቸውን በግልጽ የሚያመላክት ነው ሲሉም ተናግረዋል።
ይህም አመራሩና ህብረተሰቡ በልማቱ ላይ ሚናቸው እጅግ ከፍተኛ እንደነበር የሚያሳይ መሆኑን ተናግረው ተጠናክሮ መቀጠል ይገባዋል ብለዋል።
በአመራሩ ታታሪነትና በህብረተሰቡ ተባባሪነት በከተማው የተገነቡት የኮሪደር ልማት ስራዎች የከተማውን ገጽታ የቀየሩና ውብና ጽዱ ሆኖ እንዳገኙት የተናገሩት ደግሞ በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ሴቶች ክንፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ እሌኒ አባይ ናቸው።
የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ምክትል ፕሬዝዳንትና የጽህፈት ቤት ሃላፊ ወጣት ኡባንግ ኩመዳን በበኩላቸው በከተማው የተከናወነው የኮሪደር ልማት ቅርሶች ተጠብቀው ለትውልድ እንዲተላለፉ ባስቻለ መልኩ መሆኑን ተናግረዋል።
በብልጽግና ፓርቲ የማዕከላዊ ኢትዮዽያ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ወጣቶች ክንፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ወጣት አብዱል ድንቁ በበኩሉ በከተማው የተከናወኑት የኮሪደር ልማት ስራዎች ውብ ማራኪና የብልጽግና ጉዞን የሚያረጋግጡ ናቸው ብሏል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025