
አዳማ፤ ሰኔ 30/2017 (ኢዜአ)፦ በአዳማ ከተማ በመንግሥት በጀት እና በህዝብ ተሳትፎ የተገነቡ የተለያዩ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ተመረቁ።
የተመረቁ ፕሮጀክቶችም የዶሮና የወተት ላሞች እርባታ ማዕከላት፣ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ህንፃ፣ የወረዳ የአስተዳደር ህንፃዎች፣ የአስፋልት መንገዶች እና ሌሎችም ይገኙበታል።

የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶቹ የህዝቡን የመልማት ፍላጎት መሰረት አድርገው የተገነቡ ሲሆን የነዋሪውን የረጅም ጊዜ ጥያቄ የሚመልሱ መሆናቸውም ተገልጿል።


በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የኦሮሚያ ክልል ገጠር ክላስተር አስተባባሪ አቶ አዲሱ አረጋ፣ የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ገዛሊ አባሲመል እና የአዳማ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሃይሉ ጀልዴና ሌሎች ከፍተኛ የክልሉ የስራ ኃላፊዎችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።
ሆሳዕና ፤ ሚያዝያ 2/2018 (ኢዜአ)፦በሆሳእና፣ ወላይታ ሶዶና ቦንጋ ከተሞች በትንሳዔ በዓል ገበያ በቂ የምርትና የእርድ እንስሳት አቅርቦት መኖሩ ተመለከተ። ...
Apr 12, 2026
አዲስ አበባ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦የጉምሩክ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ የጉምሩክ አገልግሎት በሚያቀላጥፍ መልኩ እየተዘጋጀ መሆኑን በሕ...
Apr 9, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፦ የአፋር ሰመራ ሁለተኛ ደረጃ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ወደ ሥራ መግባቱ በክልሉ የሚገኘውን ሰፊ የእንስሳት ሀ...
Apr 1, 2026
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025