የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በክልሉ ስራ አጥነትን መቀነስ ታሳቢ ያደረጉና የአገልግሎት አሰጣጥን የሚያሻሽሉ የልማት ፕሮጀክቶች ለአገልግሎት እየበቁ ነው

Jul 7, 2025

IDOPRESS

ነቀምቴ፤ ሰኔ 29/2017(ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል ስራ አጥነትን መቀነስ ታሳቢ ያደረጉና የአገልግሎት አሰጣጥን የሚያሻሽሉ የልማት ፕሮጀክቶች ለአገልግሎት እየበቁ መሆኑን በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የክልሉ ከተሞች ክላስተር አስተባባሪ መስፍን መላኩ አስታወቁ።

በምስራቅ ወለጋ ዞን አንገር ጉቴ ወረዳ ከ89 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡ የተለያዩ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች የክልል፣ የዞን እና የወረዳ አመራሮች በተገኙበት ተመርቀው ለአገልግሎት በቅተዋል።


በምረቃ መርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት በምክትል ርዕስ መስተዳደር ማዕረግ የከተሞች ክላስተር አስተባባሪ ዘርፍ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ መስፍን መላኩ፣ በክልሉ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው የልማት ፕሮጀክቶች ለአገልግሎት እየበቁ ናቸው ብለዋል።

በክልሉ እየተገባደደ ባለው በጀት ዓመት በ200 ቢሊዮን ብር ግንባታቸው ሲከናወን የቆዩ ከ27 ሺህ በላይ የመሰረተ ልማት ፕሮጀከቶች ለአገልግሎት እየበቁ ናቸው ብለዋል።

በተለይም ስራ አጥነትን መቀነስ ታሳቢ ያደረጉና የአገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻል የሚያስችሉ የመሰረተ ልማት ተቋማት ለአገልግሎት እየበቁ መሆናቸውን ተናግረዋል።


ከዚህም ባሻገር የመሰረተ ልማት ተቋማቱ የህብረተሰቡን አኗኗር ማዘመን ከሚያስችሉ የልማት ስራዎች መካከል የኮሪደር ልማት ስራ በስፋት እየተከናወነ መሆኑን ጠቅሰው የመንግስት አገልግሎትን የሚያሻሽሉ የቀበሌ አደረጃጀቶችም እንዲጠናከሩ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።

በምስራቅ ወለጋ ዞን በተገኘው ሰላም በአንገር ጉቴ ወረዳ ተገንብተው ለአገልግሎት የበቁ የመሰረተ ልማት ተቋማት የዚሁ ጥረት ማሳያ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የወረዳው ነዋሪዎችም ሰላማችውን እና አንድነታችውን በመጠበቅ በልማት ስራቸው የሚያደርጉትን ተሳትፎ ማጠናከር እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።


የምስራቅ ወለጋ ዞን አስተዳደር አቶ ወጋሪ ነገራ በበኩላቸው በዞኑ በሰፈነው ሰላም የልማት ስራዎች በተሻለ መልኩ እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል።

በዞኑ በበጀት ዓመቱ በተለያዩ ወረዳዎች ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ 400 የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ግንባታ ላይ መቆየታቸውን ገልጸው ከዚህ ውስጥ 245 የሚሆኑት ተጠናቀው ለአገልግሎት እየበቁ ነው ብለዋል።

''የዞኑ አስተዳደር የህብረተሰቡን ጥያቄ ለመመለስ ቀን ከለሊት እየሰራ ይገኛል'' ያሉት አስተዳዳሪው ህዝቡም ከመንግስት ጎን በመቆም ሰላምና ጸጥታውን ማጠናከር አለበት ሲሉም ገልጸዋል።

የአንገር ጉቴ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ደረጄ በየነ፤ በወረዳው ከ89 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡ 8 የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ለአገልግሎት መብቃታቸውን ተናግረዋል።


ግንባታቸው ተጠናቆ የተመረቁ ፕሮጀክቶችም የወተት ላም እርባታ፣ የስጋ ከብት ማድለቢያ እና የዶሮ እርባታ ሼዶች፣ የቀበሌ ቤቶች፣ የኮብል ድንጋይ ንጣፍ፣ የጠጠር መንገድ እና የፈሳሽ ማስወገጃ ቦይ መገንባቱን ተናግረዋል።

የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶቹ በመንግሥት እና ከህብረተሰቡ በተገኘ በጀት መገንባታቸውን ገልፀው በፕሮጀክቶቹም 1 ሺህ 463 ሰዎች የስራ እድል ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል።


ከአንገር ጉቴ ወረዳ ነዋሪዎች መካከል የመኖሪያ ቤት የተሰጣቸው ወይዘሮ ብርሃኔ አብዲሳ፣ ከዚህ በፊት ቤታቸው ያረጀ በመሆኑ በአስቸጋሪ ሁኔታ ህይወታቸውን ሲመሩ መቆየታቸውን ተናግረዋል።


''አሁን ግን ደረጃውን የጠበቀ መኖሪያ ተገንብቶ ስለተሰጣቸው ለመንግስት ትልቅ ምስጋና አቀርባለሁ'' ብለዋል።

በፕሮጀክቶቹ ምረቃ መርሃ ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል አስተዳደር እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ኮሚሽነር አራርሳ መርዳሳን ጨምሮ ሌሎች የክልል ከፍተኛ ስራ ኃላፊዎችም ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ተቋማት ራሳቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ ይገባል- ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...

Feb 28, 2025

<p>በክልሉ የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች እየተከናወኑ ነው</p>

ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...

Feb 28, 2025

<p>ተቋማቱ በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...

Feb 28, 2025

<p>በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን ለማጠናቅ እየተሰራ ነው</p>

ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...

Feb 24, 2025