መቱ፤ ሰኔ 26/2017 (ኢዜአ)፡-በመቱ ከተማ ተገንብተው ለአገልግሎት የበቁት የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ለረጅም ጊዜ ጥያቄያቸው ምላሽ የሰጡ መሆናቸውን ነዋሪዎች ገለጹ።
በመቱ ከተማ ከ329 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ በጀት የተገነቡ የተለያዩ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ተመርቀው ለአገልግሎት በቅተዋል።
በምረቃው ወቅት ኢዜአ ያነጋገራቸው የከተማው ነዋሪዎች ፤ ለአገልግሎት የበቁት የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች የረጅም ጊዜ ጥያቄያቸውን የመለሱ እና ተጠቃሚነታቸውንም የሚያሳድጉ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ከነዋሪዎቹ መካከል አቶ ታከለ ዳዲ ፤ የተገነቡት ፕሮጀክቶች ለመሰረተ ልማት ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡ ናቸው ብለዋል።
በተለይም የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች ግንባታ ትውልዱ ከመጀመሪያ አንስቶ የተሻለ እውቀት መጨበጥ እንዲችል እድል የሚፈጥሩ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
በከተማው ለአገልግሎት የበቁ የገበያ ማዕከላት ፣ የመስሪያ እና መሸጫ ሼዶች ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴን የሚያሳድጉ በመሆናቸው ጠቀሜታቸው የጎላ ነው ብለዋል።
ሌላኛው የከተማው ነዋሪ አቶ ኦልጂራ ሂርኪሳ በበኩላቸው፤ በቀደሙት ዓመታት በከተማው የሚጀመሩ የመሰረተ ልማት ተቋማት ግንባታዎች የሚጓተቱና ተጀምረውም የሚቆሙ እንደነበሩ አስታውሰዋል።
ባለፉት ጥቂት ዓመታት ግን የከተማውን ነዋሪ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ትምህርት ቤት፣ የአገልግሎት መስጫ ማዕከላትና የመስሪያ ሼዶች በአጭር ጊዜ እየተገነቡ ለአገልግሎት እየበቁ መሆናቸውን ተናግረዋል።
የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች የነዋሪውን ተጠቃሚነት ከማሳደግ ባለፈ ለከተማዋ እድገትም ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱ ጠቅሰው ፤ ለረጅም ጊዜ አገልግሎት እንዲሰጡ መጠበቅ እና መንከባከብ ከሁላችንም ይጠበቃል ብለዋል።
በፕሮጀክቶች ምረቃ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት በብልፅግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነመራ ቡሊ፣ በክልሉ የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያግዙ የግንባታ ተግባራት የተለየ ትኩረት ተሰጥቷቸው እየተከናወኑ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በተለይም በከተሞች እየተከናወኑ የሚገኙ የመሠረተ ልማት አውታሮች ለነዋሪው የስራ ዕድል መፍጠር ጭምር የሚያስችሉ መሰረተ ልማቶች በስፋት ተጠናክረው መቀጠላቸውን ተናግረዋል።
የመቱ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ተሻለ ኤጄርሶ፤ በከተማው ከ329 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ በጀት የተገነቡ 44 የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ለአገልግሎት ክፍት መደረጋቸውን ተናግረዋል።
ፕሮጀክቶቹ የከተማ ውበትን እየጠበቁ የስራ ዕድልን መፍጠር የሚያስችሉ እንዲሁም የነዋሪዎቹን ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ መሆናቸውንም ገልጸዋል።
ዛሬ የተመረቁትም የ'ቡኡራ ቦሩ' የተሰኙ ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች፣ የከተማ ግብርና ክላስተሮች፣ የገበያ ማዕከል ሼዶችን ጨምሮ ሌሎችም የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች መሆናቸውን አስታውቀዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025