
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 26/2017(ኢዜአ)፦ በዘንድሮው ዓመት 900 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰብ መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 42ኛ መደበኛ ስብሰባውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እያካሄደ ይገኛል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በስብሰባው የመንግስትን የ2017 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃጸም አስመልክቶ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዚሁ ጊዜ ገቢን በተመለከተ በዘንድሮ አመት 900 ቢሊየን ብር ገቢ ማስገባት መቻሉን ተናግረዋል።
1 ነጥብ 2 ትሪሊየን ወጪ መውጣቱን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀው፣ በገቢና ወጭ መካከል የ300 ቢሊየን ብር ልዩነት እንዳለ ተናግረዋል።
ገቢ ግብር ብቻ ሳይሆን ልዩ ልዩ ገቢ እንዳለ የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ነገር ግን ከገቢ ግብር የተገኘው አጠቃላይ ሃብት ከወጪ አንፃር ዝቅተኛ ነው ብለዋል።
ይህ ሊሆን የቻለው ታክስ ከጥቅል ሀገራዊ ምርት ያለው ጥምርታ በአፍሪካ ስታይ 14 በመቶ መሆኑን ገልፀዋል።
ከትርፍና ከካፒታል ገቢ አንፃር ሲታይ አፍረካ ላይ 6 ነጥብ 2 በመቶ ነው ብለዋል።
የኪሳራ ሪፖርት በማቅረብ፣ ትርፍ አላገኘሁም በማለትና ሪፖርት ባለማቅረብ ምክንያት 46 ሺህ የሚጠጉ የታክስ ተመዝጋቢዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ግብር እንደማይከፍሉ አስታውቀዋል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ንግድ ፈቃድ ወስደው ግብር መክፈል ከሚገባቸው እየከፈሉ ያሉት 37 በመቶ ብቻ ናቸው ብለዋል።
እነዚህም እየከፈሉ ያሉት 60 በመቶውን ብቻ እንደሆነና ቀሪውን 40 በመቶ እየከፈሉ ያሉት የመንግስት ልማት ድርጅቶች እንደሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
ከታክስ አስተዳደር ጋር ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ሪፎርም እየተሰራ እና ለውጥ እየታየበት እንዳለ ተናግረው ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
እንዲሁም የግብር ስወራ እና ህገ ወጥ ግብይት ላይ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የሪፎርም ስራ እየተሰራ እና ለውጥ እየታየበት መሆኑን ጠቁመው ምክር ቤቱ ድጋፉን እንዲያጠናክር ጠይቀዋል።
እንዲሁም በንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ ዜጎች ግብር በታማኝነት እንዲከፍሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል።
ሆሳዕና ፤ ሚያዝያ 2/2018 (ኢዜአ)፦በሆሳእና፣ ወላይታ ሶዶና ቦንጋ ከተሞች በትንሳዔ በዓል ገበያ በቂ የምርትና የእርድ እንስሳት አቅርቦት መኖሩ ተመለከተ። ...
Apr 12, 2026
አዲስ አበባ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦የጉምሩክ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ የጉምሩክ አገልግሎት በሚያቀላጥፍ መልኩ እየተዘጋጀ መሆኑን በሕ...
Apr 9, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፦ የአፋር ሰመራ ሁለተኛ ደረጃ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ወደ ሥራ መግባቱ በክልሉ የሚገኘውን ሰፊ የእንስሳት ሀ...
Apr 1, 2026
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025