ገንዳ ውሃ፤ ግንቦት 3/2017(ኢዜአ)፡-በገንዳ ውሃ ከተማ አስተዳደር ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የጎርፍ መከላከያ ግንባታዎች እየተከናወኑ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ የቤቶች፣ ኮንስትራክሽንና መሰረተ ልማት ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
በጽህፈት ቤቱ የመሰረተ ልማት ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ታረቀኝ አለማየሁ ለኢዜአ እንደገለጹት በከተማው በጎርፍ አደጋ ተደጋጋሚ ጉዳት የሚደርስባቸውን አካባቢዎች በመለየት የጎርፍ ቅድመ መከላከል ሥራዎች እየተከናወኑ ነው።
በከተማዋ መካከል አቋርጦ የሚያልፈው የገንዳ ውሃ ወንዝ በክረምት ወቅት ሞልቶ ሲፈስ በከተማዋ በንብረትና በማሳ ላይ በተዘራ ሰብል ላይ ጉዳት ሲያደስር እንደነበረ አስታውሰዋል።
በመጪው ክረምት መሰል ችግር እንዳይከሰት ለመከላከል ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተለያዩ የጎርፍ መከላከያ ግንባታ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህም የአራት ኪሎ ሜትር የአዲስ መንገድ ከፈታ፣ የጎርፍ መፋሰሻና መቀልበሻ ትቦ ግንባታ ሥራዎች እንዲሁም የሁለት አነስተኛ ድልድዮችና መሰል ሥራዎች በመከናወን ላይ መሆናቸውን አስረድተዋል።
ከገንዳ ውሃ ከተማ ነዋሪዎች መካከል የቀበሌ 1 ነዋሪ አቶ ወንድማገኝ በየነ ባለፈው የክረምት ወቅት በደረሰ የጎርፍ አደጋ በቤታቸው ውስጥ የነበረ 10 ኩንታል አኩሪ አተር መበላሸቱን አስታውሰዋል።
የከተማ አስተዳደሩ ይሄን ችግር ተገንዝቦ ዘንድሮ የጎርፍ መውረጃ ትቦ መስራቱ ለቀጣይ ክረምት ከአደጋ ስጋት እንደታደጋቸው ተናግረዋል።
በከተማው ቀበሌ 2 የሚኖሩት ወይዘሮ ጥሩዬ አበባው በበኩላቸው እየተሰራ ያለው የጎርፍ መከላከያና መፋሰሻ ትቦ ከጎርፍ ስለሚታደጋቸው ከስጋት ነጻ መሆናቸውን ገልፀዋል።
በየዓመቱ ክረምት በመጣ ቁጥር ጭንቀት ውስጥ ይገቡ እንደነበር አስታውሰው፣ መንግስት ችግሩን ለመፍታት ባከናወናቸው የጎርፍ መከላከያ ስራዎች ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።
"ከተማ አስተዳደሩ በዚህ ዓመት አዲስ መንገድ በመክፈት በክረምት ከሚገጥም የመንገድ ችግርና የጎርፍ አደጋ ስጋት ታድጎናል" ያሉት ደግሞ የቀበሌ 01 ነዋሪ ወይዘሮ አልማዝ ገብሬ ናቸው፡፡
በአካባቢያቸው በየዓመቱ በሚከሰት የጎርፍ አደጋ በንብረት ላይ አንዳንዴም በሰው ህይወት ላይ ጉዳት ይከሰት እንደነበር አስታውሰው፣ ዘንድሮ በአካባቢያቸው የተሰራ የጎርፍ መከላከያ ከስጋት እንደታደጋቸው ተናግረዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025