ሆሳዕና፤ሚያዝያ 27/2017(ኢዜአ)፦የህዝቡን የመልካም አስተዳደር ጥያቄና የልማት ፍላጎት በአግባቡ በመገንዘብ ምላሽ መስጠት የሚችል አመራር የመፍጠር ጥረቱ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንደሻው ጣሰው (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
በተለያዩ የሃላፊነት ደረጃዎች ላይ ለሚገኙ የክልሉ አመራሮች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና በሆሳዕና ከተማ መሰጠት ተጀምሯል።
በዚሁ መድረክ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንደሻው ጣሰው (ዶ/ር)፤በዚህ ዘመን ወቅቱን የዋጀና የህዝቡን ፋላጎት በአግባቡ በመረዳት ሌት ተቀን መስራት የሚችል አመራር አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል።
ለሚያጋጥሙ ችግሮች ፈጣን መፍትሄ የሚሰጥ በእቅድ የሚመራ እና ህዝብን በቅንነት የሚያገለግል ብቁና ጠንካራ አመራር መፍጠር ይገባል ብለዋል።
የመድረኩም ዓላማ ይህንኑ መሰረት ያደረገ መሆኑን ጠቅሰው፥ አመራሩ ከመቼውም ጊዜ በላይ እውነተኛ የህዝብ አገልጋይ ለመሆን ራሱን እንዲያዘጋጅ አሳስበዋል።
በሀገሪቷ የመጣውን ለውጥ ተከትሎ በሁሉም መስኮች አስደናቂ ውጤቶች እየተመዘገቡ መሆኑን አንስተው፥ የተቀመጠውን የብልጽግና መዳረሻ ለማሳካት ከመቼውም ጊዜ በላይ የአመራሩ ቁርጠኝነት ያስፈልጋል ብለዋል።
በየደረጃው ያለው አመራር የህዝብን አቅም በማስተባበር ክልሉን ብሎም ሀገርን የሚለውጡ የልማት ስራዎችን ለማሳካት መትጋት አለበት ሲሉ ተናግረዋል።
በመድረኩ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም በየደረጃው ያሉ አመራሮች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025