
አዲስ አበባ ፤ሚያዝያ 6/2017 (ኢዜአ)፦በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራው ለወጪ ንግድ እድገት ጉልህ ሚና ማበርከቱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) ገለጹ።
የ2017 በጀት ዓመት የሦስተኛው ሩብ ዓመት የ100 ቀን አፈጻጸም እና የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ትግበራ የዘጠኝ ወራት አፈጻጸም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት ተገምግሟል።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) በሰጡት ማብራሪያ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ተጨባጭ ለውጥ እንዲያመጣ በሀገሪቱ የንግድ ካባቢ ተወዳዳሪ መሆን የሚችልበትን አቅም የመፍጠር እና የተቀላጠፈ አሰራርን የመዘርጋት ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸዋል።
በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት 2 ነጥብ 6 ሚሊየን ለሚሆኑ ዜጎች አዲስ የንግድ ፈቃድና የዕድሳት አገልግሎት መሰጠቱንም ሚኒስትሩ አብራርተዋል።
ይህም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ600 ሺህ ብልጫ ያለው መሆኑን ተናግረዋል።
በድህረ ፈቃድ ክትትልና ቁጥጥር 250 ሺህ ነጋዴዎች የንግድ ፈቃዳቸውን ከህግ አግባብ ውጭ እየተጠቀሙበት በመገኘታቸው ህጋዊ እርምጃ ተወስዶባቸዋል ነው ያሉት።
ባለፉት ዘጠኝ ወራት የተመዘገበው የወጪ ንግድ ገቢ በታሪክ ከፍተኛው መሆኑን በማንሳት፥ ለዚህም የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ትልቅ አቅም መፍጠሩን ተናግረዋል።
የምርት አቅርቦትንና ጥራትን በማሻሻል እንዲሁም የግብይት ተደራሽነትን በማስፋት የኑሮ ውድነትን ማረጋጋትና የንግዱን ዘርፍ ተወዳዳሪነት ማሳደግ ላይ አመርቂ ውጤት መገኘቱን ገልጸዋል።
የገቢና ወጪ ምርቶች ላይ ክትትልና ቁጥጥር የማድረግ አቅም 39 በመቶ እድገት ማሳየቱንም ጠቅሰዋል።
ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን የምታደርገው ድርድር ግብ እንዲመታ በትኩረት እየተሰራ እንደሆነም ጠቁመዋል።
በቀጣይ ሦስት ወራት ወጪ ንግድን ማሳደግ፣ ዲጅታላይዜሽንን ማፋጠን፣ የኢ-ኮሜርስ ስራን ተቋማዊ ማድረግ፣ የጥራት ቁጥጥርን ማጠናከር እና የአፍሪካ ነጻ ንግድ ቀጣናን ወደ ሙከራ ትግበራ ማስገባት ላይ ትኩረት ይደረጋል ብለዋል።
ሆሳዕና ፤ ሚያዝያ 2/2018 (ኢዜአ)፦በሆሳእና፣ ወላይታ ሶዶና ቦንጋ ከተሞች በትንሳዔ በዓል ገበያ በቂ የምርትና የእርድ እንስሳት አቅርቦት መኖሩ ተመለከተ። ...
Apr 12, 2026
አዲስ አበባ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦የጉምሩክ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ የጉምሩክ አገልግሎት በሚያቀላጥፍ መልኩ እየተዘጋጀ መሆኑን በሕ...
Apr 9, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፦ የአፋር ሰመራ ሁለተኛ ደረጃ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ወደ ሥራ መግባቱ በክልሉ የሚገኘውን ሰፊ የእንስሳት ሀ...
Apr 1, 2026
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025