አዲስ አበባ፤የካቲት 10/2017(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የዓለም ስልጣኔ ፈር ቀዳጅ እና በፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ላይ መገኘቷ የተመድ የዘላቂ ልማት መፍትሔ ጥምረት ለአፍሪካ ቢሮ መቀመጫነት መመረጧን የጥምረቱ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ጀፍሪ ሳክስ ገለጹ፡፡
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት(ተመድ) የዘላቂ ልማት መፍትሔ ጥምረት የአፍሪካ ቢሮውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መክፈቱን ዛሬ ይፋ አድርጓል፡፡
የተመድ የዘላቂ ልማት መፍትሔ ጥምረት ለዘላቂነት ልማት እንቅፋት የሆኑ ጉዳዮችን ለመፍታት በዓለም ዙሪያ ያሉ የፈጠራ ልሂቃንና የቴክኒክ ባለሙያዎች የሚያሰባስብ ነው፡፡
በአዲስ አበባ የተከፈተው የጥምረቱ ቢሮም የጥናትና ምርምር ሥራዎችን በማከናወን ለፖሊሲ አውጭዎች ግብዓት የሚሆኑ ሳይንሳዊ መፍትሔዎችን ያቀርባል ተብሏል።
አሜሪካዊው የምጣኔ ሀብት ባለሙያ እና የተመድ የዘላቂ ልማት መፍትሔ ጥምረት ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ጀፍሪ ሳክስ እንዳሉት፣ የጥምረቱ ተቀዳሚ ዓላማ በዓለም ላይ ኢኮኖሚያዊ ብልጽግና እና ማህበራዊ ፍትህ ማስፈን ነው።
ጥምረቱ በአሜሪካ ኒውዮርክ፤ በአውሮፓ ፓሪስ እና በኤዥያ ኳራላምፑር ቀጣናዊ ማስተባበሪያዎች እንዳሉት ገልጸው፥ አራተኛው የአፍሪካ ማስተባበሪያ ቢሮ በአዲስ አበባ ዛሬ በይፋ መከፈቱን ተናግረዋል፡፡
ኢኮኖሚያዊ እድገት፣ማሕበራዊ ፍትህ፣የአየር ንብረት ጥበቃ እና የዘላቂ የልማት ግቦች አላማዎች መሆናቸውን ገልጸዋል።
የዘላቂ ልማት መፍትሔ ጥምረት ግቡ የዘላቂ የልማት ግቦችን ማሳካት መሆኑን ገልጸው፥ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በምርምሮቻቸው፣ በአግልግሎታቸው መንግስታትን የሚደግፉ መፍትሔዎች ላይ ማተኮር አለባቸው ብለዋል፡፡
አፍሪካ በቀጣዮቹ 40 ዓመታት ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት በማስመዝገብ የዓለም ኢኮኖሚ ማዕከል ትሆናለች ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ ጥምረቱ የአፍሪካን ዘላቂ ልማትና ሰላም አጠናክሮ ማስቀጠል የሚያስችል ፕሮጀክት መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሕብረት መስራችና አባል፣ የተለያዩ ቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ ተቋማት መገኛ እንዲሁም የቀደምት ሥልጣኔ ፈር ቀዳጅ መሆኗን ተናግረዋል።
በመሆኑም ኢትዮጵያ የዓለም ስልጣኔ ፈር ቀዳጅ እና በፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ላይ መገኘቷ የተመድ የዘላቂ ልማት መፍትሔ ጥምረት ለአፍሪካ ቢሮ መቀመጫነት መርጠናታል ብለዋል፡፡
ፕሮፌሰር ጀፍሪ ሳክስ እንደ አንድ የምጣኔ ሀብት ባለሙያ በኢትዮጵያ እየተመዘገበ እንዳለው ፈጣን ኢኮኖሚያዊ እድገት የሚያስደስት ነገር የለም ብለዋል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሳሙኤል ክፍሌ(ዶ/ር) የዘላቂ የልማት ግቦች የአፍሪካ ሕብረት አጀንዳ 2063ን ከግብ ለማድረስ ቁልፍ መሳሪያ መሆኑን ተናግረዋል።
ዩኒቨርሲቲው በጥናትና ምርምር የላቀ አገልግሎት እንዳለው ገልጸው፤ የዘላቂ ልማት መፍትሔ ጥምረት ግቦችን ለማሳካት ተጨማሪ አቅም ይፈጥራል ብለዋል።
የመፍትሔ ጥምረቱ ቢሮ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መከፈቱ ትልቅ ትርጉም እንዳለው ገልጸው፤ የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማረጋገጥ የዩኒቨርሲቲውን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ለማሳደግ የጎላ አበርክቶ እንዳለውም አንስተዋል።
ዩኒቨርሲቲው በስትራቴጂክ እቅዱ ዓለም አቀፍ ትብብሮቹ ችግር ፈቺ እና ተጽዕኖ ፈጣሪ እንዲሆኑ ማስቻል ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ ከዘላቂ የልማት መፍትሔ ጥምረት ማግኘት የሚገባትን ጥቅም እንድታገኝ የሚያስችል ጥረት እንደሚያደርጉም ገልጸዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025