
አዲስ አበባ፤ የካቲት 6/2017(ኢዜአ)፦ በዕውቀትና ክህሎት የሚመራ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነትን መተግበር ለአፍሪካውያን ብልጽግና መሰረት እንደሚሆን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝደንት ሳሙኤል ክፍሌ(ዶ/ር) ገለጹ።
የአፍሪካ ልማት ባንክ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዘላቂ የልማት ማዕከል ጋር በመተባበር በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ሰምምነት ላይ ያተኮረ ሙያዊ ውይይት አካሂዷል።
በዚሁ ጊዜ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝደንት ሳሙኤል ክፍሌ(ዶ/ር)፤ አፍሪካ የሚለማ ዕምቅ የተፈጥሮ ሃብትና የሰው ሃይል ጸጋ ያላት አህጉር ናት ብለዋል።
የአውሮፓ፣ ሰሜን አሜሪካና የእስያ አህጉራት ጠንካራ የመሰረተ ልማትና የንግድ ትስስር ለሀገራቱ ኢኮኖሚያዊ አቅም መጎልበት ከፍተኛ እገዛ ማድረጉን ገልጸዋል።

በአፍሪካም የህብረቱ መስራቾች የተለሙትን ግብ ተግባራዊ በማድረግ የዜጎችን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴ ማሳለጥ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
ለዚህም የመሰረተ ልማትና የንግድ ትስስር አስፈላጊ መሆኑን ገልጸው፤ የአፍሪካን አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት በተሟላ ሁኔታ ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።
ሰላማዊት፣ የተረጋጋችና ብልጽግናዋን ያረጋገጠች አፍሪካን እውን ለማድረግም የመሪዎችን አጀንዳ ለማሳካት የአህጉሪቱ ምሁራንና የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የአህጉሪቱን ዜጎች በእውቀትና ክህሎት ለማጎልበት አፍሪካን በሁለንተናዊ መስክ ተቀራራቢና የጋራ ሥርዓተ ትምህርት ማልማት እንደሚያስፈልግም አንስተዋል።
በትብብርና መተጋገዝ ላይ የተመሰረተ ጠንካራ አህጉራዊ የትምህርትና የምርምር ተቋማትን በመገንባት በዕውቀት የሚመራ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ስምምነትን መተግበር ወሳኝ መሆኑንም ተናግረዋል።

በአፍሪካ ልማት ባንክ የቀጣናዊ ውህደት ማስተባበሪያ ቢሮ ዳይሬክተር ጆይ ካቴጌከዋ(ዶ/ር) በበኩላቸው የምንመኛትን የበለጸገች አፍሪካን ለመገንባት በትብብር መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።
ለዚህም የአፍሪካ ሀገራትን ህልም ማገናኘት ሚያስችል ጥራት ያለው የኢንዱስትሪ ምርት፣ የመሰረተ ልማት ግንባታና ትብብር እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።
የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነትም የአህጉሪቱን ምርት እሴት በመጨመር ጥራት ያለው የኢንዱስትሪያላይዜሽን ሥርዓት ለመገንባት ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ተናግረዋል።
የአፍሪካ ልማት ባንክም አህጉሪቱን በመሰረተ ልማትና በንግድ በሚያስተሳስሩ ተግባራት ላይ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ለነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት ስኬት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት ባለሙያ አንዷለም ጎሹ(ዶ/ር)፤ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት የውህደታችን ማፋጠኛ መንገድ በሚል ርዕስ የመነሻ ጽሁፍ አቅርበዋል።
በጽሁፋቸውም የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት በአጀንዳ 2063 እውን ለማድረግ ከተቀመጡ መሰረታዊ ጉዳዮች መካከል እንዱና አስፈላጊው ጉዳይ መሆኑን አስገንዝበዋል።
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 11/2018 (ኢዜአ)፦ የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ መገንባት መንግሥት የኢንዱስትሪው ዘርፍ ለሀገር ያለውን አበርክቶ ለማሳደግ በፖሊሲና ...
May 20, 2026
ድሬዳዋ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ውጤታማ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠላቸውን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ...
May 7, 2026
ደብረ ማርቆስ ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ የደብረ ማርቆስ ከተማን ባህል፣ ታሪክ ፣ ቅርስና ማህበራዊ እሴት በመጠበቅና በማልማት ለቱሪስት መስህብነት ለማዋ...
May 7, 2026
በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የአቪዬሽን ታሪክ ታይቶ የማይታወቅና በአህጉሪቱ ትልቁ የሆነውን የ12 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ግዙፍ የኤርፖርት ግንባታ ፕሮጀክት...
Apr 24, 2026