
ሀዋሳ፤ የካቲት 5/2017(ኢዜአ)፡- በሲዳማ ክልል ያሉ እምቅ ሃብቶችን በማልማት ጥቅም ላይ እንዲውሉ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና በብልጽግና ፓርቲ የሲዳማ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አብርሃም ማርሻሎ ገለጹ።
በፓርቲው ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ የተቀመጡ አቅጣጫዎችን ተግባራዊ በማድረግ ሁለንተናዊ እድገትና ብልጽግና እውን ለማድረግ በቁርጠኝነት ይሰራል ብለዋል።
በብልጽግና ፓርቲ የሲዳማ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የዞንና የወረዳ አመራሮች የፓርቲውን የሰባት ወራት አፈጻጸም በሀዋሳ ገምግመዋል።
በመድረኩ የተገኙት የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና በብልጽግና ፓርቲ የሲዳማ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አብርሃም ማርሻሎ፤ በክልሉ ያሉ እምቅ ሃብቶችን በማልማት ጥቅም ላይ እንዲውሉ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
በተለይም በለውጡ አመታት በሁሉም መስኮች የተመዘገቡ ውጤቶችን በማስቀጠል ለዜጎች ተጠቃሚነት እየተከናወኑ ያሉ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች ይከናወናሉ ነው ያሉት።
ክልሉ እምቅ የተፈጥሮ ሃብት የመልማት አቅምና ለኢንቨስትመንት ምቹ የሆኑ መልካም እድሎች ያሉት በመሆኑ ባለሃብቶች በተለያዩ ዘርፎች እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።
በሀገሪቱ ዋነኛ የእድገት መሰሶዎች ተብለው በተለዩት ዘርፎች ላይ ትኩረት በማድረግ የልማት ስራዎች በተጠናከረ መልኩ የሚቀጥሉ መሆኑንም አረጋግጠዋል።
በተለይም በግብርናው ዘርፍ ምርታማነትን በማሳደግ በምግብ ራስን ለመቻልና ከተረጅነት ለመላቀቅ የተጀመሩ ተስፋ ሰጪ ጥረቶች ይበልጥ ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።

በፓርቲው የሲዳማ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሃላፊ አስፋው ጎኔሶ፤ በፓርቲው የተቀመጡ የልማት ግቦች ያመጡትን ውጤት ለማስቀጠል በየደረጃው ያለው አመራር በቁርጠኝነት ለመፈፀም መዘጋጀቱን ገልጸዋል።
ከጥር 23 እስከ 25 ቀን 2017 ዓ.ም “ከቃል እስከ ባህል” በሚል መሪ ሐሳብ በተካሄደው የብልጽግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን እውን በማድረግ የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት ለመስራት አቅጣጫ መቀመጡ ይታወቃል።
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 11/2018 (ኢዜአ)፦ የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ መገንባት መንግሥት የኢንዱስትሪው ዘርፍ ለሀገር ያለውን አበርክቶ ለማሳደግ በፖሊሲና ...
May 20, 2026
ድሬዳዋ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ውጤታማ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠላቸውን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ...
May 7, 2026
ደብረ ማርቆስ ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ የደብረ ማርቆስ ከተማን ባህል፣ ታሪክ ፣ ቅርስና ማህበራዊ እሴት በመጠበቅና በማልማት ለቱሪስት መስህብነት ለማዋ...
May 7, 2026
በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የአቪዬሽን ታሪክ ታይቶ የማይታወቅና በአህጉሪቱ ትልቁ የሆነውን የ12 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ግዙፍ የኤርፖርት ግንባታ ፕሮጀክት...
Apr 24, 2026