
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በ2017 በጀት ዓመት ባለፋት ስድስት ወራት 169 የDNA ምርመራ ማከናወኑን ገልጿል።
ውጤቱ የተመዘገበው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዘመናዊ የDNA ምርመራ ላቦራቶሪ በማደራጀትና በዘርፉ ተገቢው ሙያዊ ዕውቀት ያላቸው ባለሙያዎችን በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር አሰልጥኖ ወደ ሥራ በማሰማራቱ መሆኑን ተቋሙ አስታውቋል።

ከለውጡ በፊት በሀገር ውስጥ የDNA ምርመራ አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም ባለመኖሩ ናሙና ወደ ውጭ ሀገር እየተላከ በከፍተኛ ወጪ ሲመረመር እንደነበር አስታውሶ ይህን አሠራር በማስቀረት በሀገር ውስጥ የDNA የምርመራ አገልግሎት መስጠት መቻሉን ገልጿል፡፡
የDNA ምርመራ ለፍትህ ሥርዓት መረጋገጥ ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሶ በተለይ የሰዎችን ማንነት ለመለየት፤ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ለማረጋገጥ፣ ከተወላጅነት ጋር ለሚነሱ ክርክሮችና ቤተሰባዊ ጉዳዮችን ለመመርመር የሚያስችል አቅም እንደተፈጠረም ከተቋሙ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 11/2018 (ኢዜአ)፦ የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ መገንባት መንግሥት የኢንዱስትሪው ዘርፍ ለሀገር ያለውን አበርክቶ ለማሳደግ በፖሊሲና ...
May 20, 2026
ድሬዳዋ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ውጤታማ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠላቸውን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ...
May 7, 2026
ደብረ ማርቆስ ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ የደብረ ማርቆስ ከተማን ባህል፣ ታሪክ ፣ ቅርስና ማህበራዊ እሴት በመጠበቅና በማልማት ለቱሪስት መስህብነት ለማዋ...
May 7, 2026
በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የአቪዬሽን ታሪክ ታይቶ የማይታወቅና በአህጉሪቱ ትልቁ የሆነውን የ12 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ግዙፍ የኤርፖርት ግንባታ ፕሮጀክት...
Apr 24, 2026