የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

<p>ሀገር በቀል ዕውቀቶች ለሰላምና አብሮነት ያላቸውን አበርክቶ ለማጎልበት ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው</p>

Feb 7, 2025

IDOPRESS

ዲላ፤ ጥር 29/ 2017(ኢዜአ)፦ ሀገር በቀል ዕውቀቶች ለሀገራዊ ሰላም፣ አብሮነት እና ለሥራ ፈጠራ ያላቸውን አበርክቶ ለማጎልበት ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

"ሀገር በቀል እውቀት ለሀገራዊ ልማት" በሚል መሪ ቃል 7ኛው ሀገራዊ የሀገር በቀል ዕውቀት ዐውደ ጥናት በዲላ ዩኒቨርሲቲ ተካሂዷል።

በዐውደ ጥናቱም ሀገር በቀል ዕውቀትን መሰረት ያደረጉ 10 የምርምር ውጤቶች በምሁራን ቀርበው ውይይት ተደርጓባቸዋል።

በሚኒስቴሩ የባህል እሴቶችና ሀገር በቀል እውቀቶች ሥራ አስፈጻሚ ወይዘሮ እስከዳር ግሩም ለኢዜአ እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ የበዙ ባህላዊና ሀገር በቀል እውቀቶች ባለቤት ናት።

ለዚህም የዕደ ጥበብ ውጤት፣ የግጭት አፈታት ሥርዓት፣ የዘመን አቆጣጠር እንዲሁም የባህል ህክምና፣ የእርከንና የግብርና ልማት ተጠቃሽ ሀገር በቀል እውቀቶች መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

የለውጡ መንግስት ለባህል እሳቤዎች ትኩረት መስጠቱ ሀገር በቀል እውቀቶች በምርምር እንዲዳብሩ አቅም መፍጠሩን ጠቅሰዋል።

ይህን ለማጠናከር በተለይ ሀገር በቀል እውቀት ለሀገራዊ ሰላም፣ አንድነትና ለሥራ ዕድል ፈጠራ ያለውን አበርክቶ ለማጠናከር ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ገለጸዋል።

የጌዴኦ የዘመን መለወጫ የዳራሮ በዓልን ምክንያት በማድረግ አውደ ጥናቱ በየዓመቱ እንደሚዘጋጅ ያነሱት ደግሞ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ኤልያስ ዓለሙ ናቸው።

ዩኒቨርሲቲው የሀገር በቀል እውቀቶችን ለማበልጸግ ትምህርትና ስልጠና ከመስጠት ባለፈ የተለያዩ ጥናትና ምርምሮችን በጋራና በተናጠል እያከናወነ ይግኛል ብለዋል።

በዚህም ሀገር በቀል እውቀቶች ከትምህርት አልፎ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ውስጥ የጎላ ሚና እንዲኖራቸው ዩኒቨርሲቲው እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ለሀገር በቀል እውቀቶች የተሰጠው ትኩረት ለሰላምና ለአንድነት ቅድሚያ የሚሰጥ ማህበረሰብ ለመፍጠር የራሱ ፋይዳ እንዳለው ጠቁመዋል።

የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶክተር ዝናቡ ወልዴ በበኩላቸው በዩኔስኮ የተመዘገበው የጌዴኦ የተፈጥሮ መልክዓ ምድር የሀገር በቀል እውቀት ትሩፋት መሆኑን ጠቅሰዋል።

ሀገር በቀል እውቀት ለማህበረሰቡ ቅርብና ለመረዳት ቀላይ በመሆኑ ተመራጭ መሆኑን ጠቅሰው፣ ለትውልድ እንዲሸጋገር የመንከባከብና የመጠበቅ ሥራ ይሰራል ብለዋል።

ባህላዊ እውቀትን በአግባቡ ሰንዶ ለማቆየት በሚሰራው ሥራ አውድ ጥናቱ ሚናው የጎላ መሆኑንም ጠቁመዋል።

በአውደ ጥናቱ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የመጡ ምሁራን፣ ተመራማሪዎች የባህል ሽማግሌዎችና የዘርፉ ባለድርሻ አካላት እንዲሁም የተለያዩ የሥራ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኢንዱስትሪ ፓርኩ መገንባት መንግሥት ለዘርፉ የሰጠውን ትኩረት በተጨባጭ ያረጋገጠ ነው

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 11/2018 (ኢዜአ)፦ የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ መገንባት መንግሥት የኢንዱስትሪው ዘርፍ ለሀገር ያለውን አበርክቶ ለማሳደግ በፖሊሲና ...

May 20, 2026

የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ውጤታማ ተግባራት ተጠናክረው ቀጥለዋል 

ድሬዳዋ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ውጤታማ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠላቸውን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ...

May 7, 2026

የከተማዋን ባህል፣ ታሪክ፣ ቅርስና ማህበራዊ እሴት በማልማት ለኢኮኖሚያዊ ጥቅም የማዋል ተግባራት ይጠናከራሉ

ደብረ ማርቆስ ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ የደብረ ማርቆስ ከተማን ባህል፣ ታሪክ ፣ ቅርስና ማህበራዊ እሴት በመጠበቅና በማልማት ለቱሪስት መስህብነት ለማዋ...

May 7, 2026

ከአፍሪካ አቪዬሽን መሪነት እስከ አህጉራዊ የኢኮኖሚ ትስስር

በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የአቪዬሽን ታሪክ ታይቶ የማይታወቅና በአህጉሪቱ ትልቁ የሆነውን የ12 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ግዙፍ የኤርፖርት ግንባታ ፕሮጀክት...

Apr 24, 2026