የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

<p>በክልሉ 4 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጠ</p>

Feb 6, 2025

IDOPRESS

ቦንጋ ፤ጥር 28/2017 (ኢዜአ)፡-በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ባለፉት ስድስት ወራት ከ4 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፍቃድ መሰጠቱ ተገለጸ።

እየተካሄደ በሚገኘው የክልሉ መንግስት የ6 ወራት የስራ አፈፃፀምና የፓርቲ ስራዎች የግምገማ መድረክ የኢንቨስትመንት አፈጻጸምም ቀርቧል።

የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ሰለሞን በቀለ ባቀረቡት ሪፖርት እንዳሉት በክልሉ የኢንቨስትመንት ጥያቄዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል።


በዚህም በበጀት ዓመቱ ባለፉት ስድስት ወራት 4 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ 54 ባለሀብቶች ፍቃድ መሠጠቱንም ገልፀዋል።

ፈቃድ የተሰጠውም በግብርና፣ በኢንዱስትሪና በአገልግሎት ዘርፍ መሆኑን ጠቁመዋል።

እንዲሁም 7 ሺህ 635 ሄክታር የኢንቨስትመንት መሬት የመለየት ስራ መሠራቱንም ተናግረዋል።

ምቹ ሁኔታዎችን ከመፍጠር አኳያም ባለሀብቶችን በማስተባበር 55 ኪሎ ሜትር መዳረሻ መንገድ ግንባታ ማካሄድ እንደተቻለም ጠቁመዋል።

በነዚህ ወራት በክልሉ ለተለያዩ ፕሮጀክቶች 10 ሺህ 435 ሄክታር መሬት ማስተላለፍ መቻሉንም ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም የኢንቨስትመንት ፈቃድ የወሰዱ 70 ድርጅቶች ላይ የመሬት ኦዲት በማድረግ ወደ ስራ ያልገባ 10 ሺህ 295 ሄክታር መሬት ወደ መሬት ባንክ ገቢ መደረጉንም አንስተዋል።

በተመሳሳይ በክልሉ ባለፉት ስድስት ወራት ከ25 ሺህ ቶን በላይ የታጠበ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ የቀረበ ሲሆን፣ ይህም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 24 ነጥብ 9 በመቶ ብልጫ እንዳለው ተናግረዋል።

በተጨማሪም 21 ሺህ 877 ቶን የተለያየ ቅመማ ቅመም ምርት ለገበያ መቅረቡንም አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኢንዱስትሪ ፓርኩ መገንባት መንግሥት ለዘርፉ የሰጠውን ትኩረት በተጨባጭ ያረጋገጠ ነው

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 11/2018 (ኢዜአ)፦ የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ መገንባት መንግሥት የኢንዱስትሪው ዘርፍ ለሀገር ያለውን አበርክቶ ለማሳደግ በፖሊሲና ...

May 20, 2026

የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ውጤታማ ተግባራት ተጠናክረው ቀጥለዋል 

ድሬዳዋ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ውጤታማ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠላቸውን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ...

May 7, 2026

የከተማዋን ባህል፣ ታሪክ፣ ቅርስና ማህበራዊ እሴት በማልማት ለኢኮኖሚያዊ ጥቅም የማዋል ተግባራት ይጠናከራሉ

ደብረ ማርቆስ ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ የደብረ ማርቆስ ከተማን ባህል፣ ታሪክ ፣ ቅርስና ማህበራዊ እሴት በመጠበቅና በማልማት ለቱሪስት መስህብነት ለማዋ...

May 7, 2026

ከአፍሪካ አቪዬሽን መሪነት እስከ አህጉራዊ የኢኮኖሚ ትስስር

በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የአቪዬሽን ታሪክ ታይቶ የማይታወቅና በአህጉሪቱ ትልቁ የሆነውን የ12 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ግዙፍ የኤርፖርት ግንባታ ፕሮጀክት...

Apr 24, 2026