
አዲስ አበባ፤ ጥር 12/2017(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን መቋቋም የሚችል ስርዓተ-ምግብ ለመፍጠር የሰጠችው ትኩረት ውጤት እያስገኘ መሆኑን የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ማንደፍሮ ንጉሤ(ዶ/ር) ገለጹ።
ዋና ዳይሬክተሩ ለኢዜአ እንደገለጹት ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ ለመገንባት የተለያዩ ስራዎች እያከናወነች ትገኛለች።
በተለይም ባለፉት አራት ዓመታት ግብርናውን ለማዘመንና የምግብ ዋስትና እና የስርዓተ ምግብ ሽግግርን ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ አሰራርን የበለጠ የሚያጠናክር የሚኒስትሮች ዐቢይ ኮሚቴ ተቋቁሞ የተለያዩ ስራዎችን እየተሠሩ መሆኑን አመልክተዋል።
ይህንን ተከትሎ ዓለም አቀፍ ተጽዕኖ የሆነው የአየር ንብረት ለውጥ ኢትዮጵያ ግብርና ላይ ሊያደርስ የሚችለውን ጉዳት ለመቀነስ የተሰሩ ስራዎች መሰራታቸውን አስታውቀዋል፡፡
በመስኖ ልማት፣ በሌማት ትሩፋት፣ በአረንጓዴ አሻራ የስርዓተ ምግብ ሽግግርን የሚያፋጥኑ ተጨባጭ ውጤቶች መገኘታቸውን ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
እነዚህም መንግስት ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ስርዓተ ምግብ ለመፍጠር ተግባራዊ ምላሽ መስጠቱን ዐቢይ ማሳያ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
በኢንስቲትዩቱ የኢትዮጵያ ምግብ ስርዓት ትራንስፎርሜሽን እና ኒዉትሪሽን አስተባባሪ ጌታቸው ድሪባ (ዶ/ር) በበኩላቸው፥ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ተጋላጭነትን የሚቀንሱ ተግባራት እየተከናወኑ ነው ብለዋል።

ባለፉት ዓመታት ግብርናውን ለማዘመን፣ ዓይነተ ብዙ ምግብ ለማምረት፣ በንጥረ ምግብ የበለጸጉ ምግቦችን ለማቅረብ የተጀመሩ ስራዎች የተሻለ ውጤት እያስገኙ መሆኑን የስራ ኃላፊዎቹ አንስተዋል፡፡
በቀጣይም የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን የበለጠ ለመቋቋም በግብርናው ዘርፍ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማስፋት እንደሚገባም አመላክተዋል።
ቅንጅታዊ አሰራርን የበለጠ ማጠናከርና የዘርፎችን ትስስር ማጎልበትም ሌላኛው ወሳኝ የቤት ሥራ ነው ብለዋል።
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 11/2018 (ኢዜአ)፦ የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ መገንባት መንግሥት የኢንዱስትሪው ዘርፍ ለሀገር ያለውን አበርክቶ ለማሳደግ በፖሊሲና ...
May 20, 2026
ድሬዳዋ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ውጤታማ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠላቸውን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ...
May 7, 2026
ደብረ ማርቆስ ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ የደብረ ማርቆስ ከተማን ባህል፣ ታሪክ ፣ ቅርስና ማህበራዊ እሴት በመጠበቅና በማልማት ለቱሪስት መስህብነት ለማዋ...
May 7, 2026
በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የአቪዬሽን ታሪክ ታይቶ የማይታወቅና በአህጉሪቱ ትልቁ የሆነውን የ12 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ግዙፍ የኤርፖርት ግንባታ ፕሮጀክት...
Apr 24, 2026