
አዲስ አበባ፤ ጥር 13/2017(ኢዜአ)፦ለ2017/18 የምርት ዘመን የአፈር ማዳበሪያ ኦፕሬሽን የሚውል 313 ሺህ 260 ሜትሪክ ቶን የዩሪያ እና ዳፕ ማዳበሪያ የጫኑ ስድስት መርከቦች ጅቡቲ ወደብ መድረሳቸው ተገለጸ።
የምርት ዘመኑ የአፈር ማዳበሪያ ኦፕሬሽን ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።
እስከ አሁን 313 ሺህ 260 ሜትሪክ ቶን የዩሪያ እና ዳፕ ማዳበሪያ የጫኑ ስድስት መርከቦች ጅቡቲ ወደብ መድረሳቸውንና ከዚህ ጭነት ውስጥ 256 ሺህ 398 ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ወደ ኢትዮጵያ መላኩን ገልጿል።
ቀሪው ማዳበሪያ በመጓጓዝ ላይ እንደሚገኝም ነው የጠቆመው።

በተጨማሪም 56 ሺህ ሜትሪክ ቶን ዳፕ የአፈር ማዳበሪያ የጫነች ሰባተኛ መርከብ ትናንት ዶራሌ ሁለገብ ወደብ ደርሳ ጭነት በማራገፍ ላይ መሆኗንም አመልክቷል።
በሚቀጥሉት ቀናትም ተጨማሪ አራት አፈር ማዳበሪያ የጫኑ መርከቦች ጂቡቲ ይደርሳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም አስታውቋል።

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 11/2018 (ኢዜአ)፦ የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ መገንባት መንግሥት የኢንዱስትሪው ዘርፍ ለሀገር ያለውን አበርክቶ ለማሳደግ በፖሊሲና ...
May 20, 2026
ድሬዳዋ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ውጤታማ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠላቸውን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ...
May 7, 2026
ደብረ ማርቆስ ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ የደብረ ማርቆስ ከተማን ባህል፣ ታሪክ ፣ ቅርስና ማህበራዊ እሴት በመጠበቅና በማልማት ለቱሪስት መስህብነት ለማዋ...
May 7, 2026
በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የአቪዬሽን ታሪክ ታይቶ የማይታወቅና በአህጉሪቱ ትልቁ የሆነውን የ12 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ግዙፍ የኤርፖርት ግንባታ ፕሮጀክት...
Apr 24, 2026