
ሠመራ፤ ጥር 7/2017(ኢዜአ)፡- በምንከፍለው ግብር ለህዝብ አገልግሎት የሚውሉ መሠረተ ልማቶች የሚገነቡ መሆናቸውን በመገንዘባችን ግብራችንን በወቅቱ ከፍለናል ሲሉ የአፋር ክልል ግብር ከፋዮች ገለጹ።
በክልሉ የሠመራ ሎጊያ ከተማ ነዋሪ የሆኑት ግብር ከፋይ አቶ አንዋር መኮንን እንዳሉት እኛ የምንከፍለው ግብር መልሶ ለህዝብ ጥቅም የሚውሉ ልማቶች በጊዜያቸው እንዲጠናቀቁ ያደርጋል።
በዚሁ ግንዛቤ ግብራቸውን በጊዜው በመክፈላቸው የተለያዩ መሠረተ ልማቶች እንዲሟሉ ከማድረግ ባለፈ ለሀገር እድገት የራሳቸውን ሃላፊነት በወቅቱ እንዲወጡ እንዳስቻላቸውም ተናግረዋል።
ግብር በመክፈላቸው መንገዶች፣ ጤና ተቋማት እና ትምህርት ቤቶች እንዲገነቡ ዕድል የሚሰጥ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ ሌላው ግብር ከፋይ አቶ አወል ኢድሪስ ናቸው።
በመሆኑም ሁሉም ሰው የሚጠበቅበትን ግብር በወቅቱ እንዲከፍል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የክልሉ ገቢዎች ቢሮ በበኩሉ ባለፉት ስድስት ወራት ከ2 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሠብሰቡን ገልጿል።
የቢሮው ሃላፊ አቶ አወል አብዱ ለኢዜአ እንደገለፁት በ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት በግማሽ መጀት ዓመቱ 2 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ ወደ ሥራ ተገብቷል።
ከዚህም 2 ቢሊዮን 671 ሚሊዮን 393ሺህ አራት ብር መሠብሰቡን ገልጸው፤ በዚህም የዕቅዱን 97 በመቶ ማከናወን መቻሉን ተናግረዋል።
ይኸም ባለፈው ዓመት ተመሣሣይ ወቅት ከተሰበሰበው ጋር ሲነፃፀር ከ794 ሚሊየን ብር በላይ ብልጫ ያለውና በመቶኛም የ42 በመቶ ብልጫ የታየበት መሆኑን አስረድተዋል።
እንደ ሃላፊው ገለጻ፤ የተሻለ አፈጻጸም ሊኖር የቻለው በወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች ላይ የግንዛቤ ማሣደጊያ ስራዎች በመከናወናቸውና ባለሙያዎችም በቁርጠኝነት በመሥራታቸው ነው።
ይህም ሆኖ ከደረሠኝ አሰጣጥና አቆራረጥ ጋር አሁንም የሚስተዋሉ ችግሮች መኖራቸውን ጠቅሰው፤ በዚህ ረገድ ሃላፊነታቸውን በማይወጡ ግብር ከፋዮች ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ተናግረዋል።
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 11/2018 (ኢዜአ)፦ የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ መገንባት መንግሥት የኢንዱስትሪው ዘርፍ ለሀገር ያለውን አበርክቶ ለማሳደግ በፖሊሲና ...
May 20, 2026
ድሬዳዋ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ውጤታማ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠላቸውን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ...
May 7, 2026
ደብረ ማርቆስ ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ የደብረ ማርቆስ ከተማን ባህል፣ ታሪክ ፣ ቅርስና ማህበራዊ እሴት በመጠበቅና በማልማት ለቱሪስት መስህብነት ለማዋ...
May 7, 2026
በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የአቪዬሽን ታሪክ ታይቶ የማይታወቅና በአህጉሪቱ ትልቁ የሆነውን የ12 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ግዙፍ የኤርፖርት ግንባታ ፕሮጀክት...
Apr 24, 2026