
አዲስ አበባ፤ ጥር 5 /2017 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ ከዩኤን ሀቢታት ጋር ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች ላይ ያላትን ትብብር አጠናክራ እንደምትቀጥል የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ ገለፁ።
ሚኒስትሯ ጫልቱ ሳኒ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ሰፈራ መርሃ-ግብር (ዩኤን ሀቢታት) የአፍሪካ ቀንድ እና የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ኢስሃኩ ማቱምቢ ጋር ተወያይተዋል።
ሚኒስትሯ በኢትዮጵያና በቀጣናው አገራት የተከናወኑ ስራዎችና በመልካም ተሞክሮ መቀመር አስፈላጊነት ላይ ውይይት መደረጉን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።
የዩኤን ሃቢታት ቀጣይ ስትራቴጂካዊ ትኩረት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሞችና አገራዊ የልማት ስትራቴጂክ ዕቅድ ጋር የተጣጣመ እንዲሆን እንደሚሰራ አመልክተዋል።
በቀጣይም ሁለቱ ወገኖች በሀገራዊ፤ ቀጣናዊና አህጉራዊ ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት መስማማታቸውንም ጠቁመዋል።
በሌላ በኩል ኢትዮጵያ በቀጣይ መጋቢት ወር ለዩኤን ሀቢታት ስራ አስፈጻሚ ቦርድ ለምታቀርበው የመልካም ተሞክሮና የከተማ ልማት የመሪነት ሚና ዝግጅት መጀመሯን ለዳይሬክተሩ መግለጻቸውን ነው ሚኒስትሯ በመልዕክታቸው ላይ ያሰፈሩት።
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 11/2018 (ኢዜአ)፦ የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ መገንባት መንግሥት የኢንዱስትሪው ዘርፍ ለሀገር ያለውን አበርክቶ ለማሳደግ በፖሊሲና ...
May 20, 2026
ድሬዳዋ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ውጤታማ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠላቸውን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ...
May 7, 2026
ደብረ ማርቆስ ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ የደብረ ማርቆስ ከተማን ባህል፣ ታሪክ ፣ ቅርስና ማህበራዊ እሴት በመጠበቅና በማልማት ለቱሪስት መስህብነት ለማዋ...
May 7, 2026
በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የአቪዬሽን ታሪክ ታይቶ የማይታወቅና በአህጉሪቱ ትልቁ የሆነውን የ12 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ግዙፍ የኤርፖርት ግንባታ ፕሮጀክት...
Apr 24, 2026