🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 24/2018 (ኢዜአ)፦ ሀገራዊ ለውጡ የሀገሪቱን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ስብራቶች በመጠገን፣ ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ከፍታና ለማህበራዊ ትስስር ጽኑ መሰረት መጣሉን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ዛሬ መጋቢት 24 ቀን በጉለሌ ክፍለ ከተማ 6ተኛውን አዲስ መሶብ ዲጂታል አንድ ማዕከል በይፋ መርቀዋል።

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት መጋቢት 24 ቀን ኢትዮጵያን ወደ አዲስ ምዕራፍ ለማሻገር ቃል ኪዳን የተገባበት ታሪካዊ ቀን ነው።
ሀገራዊ ለውጡ የመጣው ለሁሉም፣ ከሁሉምና በሁሉም ዜጋ ተሳትፎ መሆኑን የገለጹት ከንቲባዋ፤ ከለውጡ ወዲህ የሚታዩና ተጨባጭ የሆኑ በርካታ ስኬቶች የተመዘገቡት በጋራ ጥረታችን ነው ብለዋል።
ይህ ለውጥ የፖለቲካ፣ የማህበራዊና የኢኮኖሚ ስብራቶቻችን እንዲጠገኑና ወደ ከፍታ እንድንጓዝ እጅግ ጠንካራ መሰረት የጣለ ነው ሲሉም ገልጸዋል።
ባለፉት ዓመታት “እንሰራለን፤ እንችላለን!” በሚል መርህ በጋራ በተነሳንባቸው ጊዜያት፣ ከኋላ ቀር የፖለቲካ ባህሎች ተላቀን ችግሮችን በውይይትና በምክክር የመፍታት ሂደት ላይ መገባቱን ከንቲባዋ አመልክተዋል።
ባለፉት ስምንት ዓመታት የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ሽግግር ወደ ዘመናዊ እና ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚ ለመገንባት በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ በርካታ ስኬቶች መመዝገባቸውንም ነው ያነሱት።
በማህበራዊ ዘርፍም የተሰበሩ እሴቶችን በማከም ማህበራዊ ፍትህ እንዲነግስ የሚስችሉ በርካታ ውጤቶች መገኘታቸውን ተናግረዋል።
በተለይም በከተማዋ የሚገኙ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ወገኖችን፣ የሀገር ባለውለታዎችን፣ አቅመ ደካሞችን፣ አካል ጉዳተኞችንና ረዳት የሌላቸውን ወገኖች ከአስቸጋሪ ኑሮ አውጥተን የሰውን ክብር በሚመጥን መልኩ እንዲኖሩ አድርገናል ብለዋል።
በትምህርት ዘርፍም ባዶ ምሳ ዕቃ ይዘው ወደ ትምህርት ገበታ ይመጡ የነበሩ ሕፃናትን እኩል በልተውና ለብሰው እንዲማሩ ከማድረግ ባለፈ፣ አዲስ አበባን ሕፃናትን ለማሳደግ ተመራጭ ከተማ ለማድረግ መቻሉን በመልዕክታቸው ጠቁመዋል።
ሌላው ትልቅ ስኬት የመንግስት የተቋማት ስብራትን በመጠገን ነፃ፣ ገለልተኛና የአገልጋይነት መንፈስን የተላበሱ ጠንካራ ተቋማትን የመገንባት ሽግግር መሆኑን ገልጸዋል።
ለዘመናት የአገልግሎት ዘርፉን ለመለወጥ ሳይቻል ስር በሰደደ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር ተተብትቦ የኖረ ቢሆንም፣ የለውጡ መንግስት ቃል በገባው መሰረት ችግሩን ሥር ነቀል በሆነ መልኩ የሚለውጥ 'መሶብ' ዲጂታል አንድ ማዕከልን በመተግበር ለተገልጋዩ እፎይታን ይዞ መምጣቱን አመልክተዋል።
የእነዚህ የለውጥ ፍሬዎች ዋንኛ ተጠቃሚ የሆነው የአዲስ አበባ ነዋሪም ማልዶ ወደ አደባባዮች በመውጣት የዘወትር ድጋፉን እንደገና ማጽናቱን ከንቲባዋ ተናግረዋል።
ጅማሬያችን ትላንት ቢሆንም ከህዝባችን ጋር ያሳካነው ድል እና የደረስንበት ርቀት ቀላል አይደለም ሲሉም አክለዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ የኢትዮጵያን የብልፅግና ጉዞ ሊያስቆም የሚችል ምንም ዓይነት ምድራዊ ኃይል እንደሌለ በመልዕክታቸው ላይ አስፍረዋል።
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 24/2018 (ኢዜአ)፦ ሀገራዊ ለውጡ የሀገሪቱን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ስብራቶች በመጠገን፣ ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ከፍታና ለማህበራዊ ትስስ...
Apr 3, 2026
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025