🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 18/2018 (ኢዜአ)፡- አምራች ኢንዱስትሪዎች የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ከማሳደግ ባለፈ የንግድ ሚዛንን በማስጠበቅ ረገድ የጎላ ሚና እየተጫወቱ መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ታረቀኝ ቡሉልታ ገለፁ።
የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች በአዲስ አበባ እና በሸገር ከተማ የሚገኙ በጨርቃ ጨርቅና አልባሳት፣ በቆዳ፣ በምግብ፣ በኤሌክትሮኒክስ እና በሶላር ሴል አምራች ዘርፎች የተሰማሩ ፋብሪካዎችን ጎብኝተዋል።

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ታረቀኝ ቡሉልታ በዚሁ ወቅት፤ ከለውጡ ወዲህ ለሀገር ብልጽግና፣ ዕድገትና ተወዳዳሪነት የአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ እንደ ዋና ምሰሶ ተለይቶ ትኩረት ተሰጥቶታል ብለዋል።
በአገልግሎት አሰጣጥ፣ በመሠረተ ልማት፣ በፋይናንስ አቅርቦት ዙሪያ የነበሩ ክፍተቶች እንዲቀረፉ በመደረጉ ለአምራች ኢንዱስትሪ ምቹ ሁኔታ መፈጠሩንም ተናግረዋል።
በአሁኑ ወቅት 45 ነጥብ 3 በመቶ የምርት ፍላጎት በሀገር ውስጥ ምርቶች እየተሸፈነ መሆኑን ገልጸዋል።
የወጪ ምርቶች በመጠንም በጥራትም በማደጋቸው የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ከማሳደግ ባለፈ የንግድ ሚዛንን በማስጠበቅ ረገድ የጎላ ሚና እየተጫወቱ መሆኑንም አመላክተዋል።
የዘርፉን ስኬቶች ለሕዝብ ተደራሽ በማድረግ እና ያሉ ተግዳሮቶችን በማመላከት ረገድ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት እያደረጉት ያለውን ሥራ አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጥሪ አቅርበዋል።
ሀዋሳ፤ ግንቦት 6/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ እየተከናወኑ ያሉ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች ከተረጅነት የመውጣት ጥረትን ለማሳካት የሚያስችል ተጨባጭ ውጤት እያመ...
May 15, 2026
ጅግጅጋ፤ ሚያዝያ 13/2018 (ኢዜአ)፦ በኦዲት ዘርፍ በተከናወኑ የሪፎርም ተግባራት ተጨባጭ ለውጦች እየተመዘገቡ መሆናቸውን የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሠረት ዳምጤ...
Apr 22, 2026
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 7/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በምግብ ዋስትና እና በኢኮኖሚ ልማት ዘርፍ እያከናወነቻቸው ያሉ ተግባራት ለመላው አፍሪካ አገራት ትልቅ አ...
Apr 16, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 24/2018 (ኢዜአ)፦ ሀገራዊ ለውጡ የሀገሪቱን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ስብራቶች በመጠገን፣ ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ከፍታና ለማህበራዊ ትስስ...
Apr 3, 2026