🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እና ሳዑዲ አረቢያ በንግድና ገበያ ዕድል ድርድር ዙሪያ ምክክር አድርገዋል።
14ኛው የዓለም ንግድ ድርጅት(WTO) የሚኒስትሮች ጉባኤ (MC14) በካሜሮን ያውንዴ እየተካሄደ ይገኛል።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) ከጉባኤው ጎን ለጎን ከሳዑዲ አረቢያ የዓለም አቀፍ ስምምነቶችና ድርጅቶች ምክትል ገዥ እና የድርድር ቡድን መሪ ፋሪድ አል-አሳሊ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።

ውይይቱ በዋናነት ያተኮረው በሁለቱ ሀገራት መካከል ባለው የገበያ ዕድል ድርድርና የንግድ ልውውጥን ይበልጥ ማሳደግ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ነው።
ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ወደ ዓለም ንግድ ድርጅት ለመቀላቀል የምታደርገውን ድርድር በፈረንጆቹ 2026 ለማጠናቀቅ ያላትን ጽኑ አቋምና ዝግጁነት አብራርተዋል።
ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን የምታደርገው ጥረት ማጠናቀቂያው ላይ በደረሰበት በዚህ ወቅት፣ እንደ ሳዑዲ አረቢያ ካሉ ጠንካራ የንግድ አጋሮች ጋር የሚደረጉ የሁለትዮሽ ድርድሮች ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገትና ለንግድ ስርዓቱ መዘመን ትልቅ ፋይዳ እንዳላቸው ተገልጿል።

በመጪው ሚያዚያ ወር በጄኔቫ ከሚካሄደው የሥራ ቡድን ስብሰባ በፊት የሁለትዮሽ የገበያ ዕድል ስምምነቱን ለማጠናቀቅ ቀጣይ የቴክኒክ ድርድሮች በፍጥነት እንዲከወኑ በሁለቱ ወገኖች መካከል መግባባት ላይ ተደርሷል።
ዲፕሎማሲያዊ ጥረቱ ኢትዮጵያ ወደ ዓለም አቀፍ የንግድ ሥርዓት ለመቀላቀል የምታደርገውን ጉዞ የሚያፋጥንና የሀገሪቱን የንግድ ጥቅሞች ይበልጥ የሚያረጋግጥ መሆኑን ኢዜአ ከንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ሀዋሳ፤ ግንቦት 6/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ እየተከናወኑ ያሉ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች ከተረጅነት የመውጣት ጥረትን ለማሳካት የሚያስችል ተጨባጭ ውጤት እያመ...
May 15, 2026
ጅግጅጋ፤ ሚያዝያ 13/2018 (ኢዜአ)፦ በኦዲት ዘርፍ በተከናወኑ የሪፎርም ተግባራት ተጨባጭ ለውጦች እየተመዘገቡ መሆናቸውን የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሠረት ዳምጤ...
Apr 22, 2026
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 7/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በምግብ ዋስትና እና በኢኮኖሚ ልማት ዘርፍ እያከናወነቻቸው ያሉ ተግባራት ለመላው አፍሪካ አገራት ትልቅ አ...
Apr 16, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 24/2018 (ኢዜአ)፦ ሀገራዊ ለውጡ የሀገሪቱን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ስብራቶች በመጠገን፣ ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ከፍታና ለማህበራዊ ትስስ...
Apr 3, 2026