🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 12/2018 (ኢዜአ)፡- የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር የኢትዮጵያን የደን ሽፋን በማሳደግ ዘርፈ-ብዙ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳዎችን እያበረከተ መሆኑን የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ አስገነዘቡ።
የፌዴራልና የክልል የግብርና ዘርፍ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ''የመደመር መንግሥት የተፈጥሮ ሃብት ዕይታ'' በሚል መሪ ሐሳብ የዓለም የደን ቀንን አስመልክቶ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው።

ሚኒስትር አዲሱ አረጋ በዚሁ ወቅት፤ የመደመር መንግሥት ለአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር የሰጠው ትኩረት የተፈጥሮ ሃብቶችን በማስጠበቅ ዘርፈ-ብዙ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ማበርከት ያስቻሉ ውጤቶች ማስገኘቱን አስገንዝበዋል።
በዚህም ባለፉት የለውጥ ዓመታት ከ48 ቢሊየን በላይ ችግኞችን በመትከል የኢትዮጵያን የደን ሽፋን ከነበረበት የ17 ነጥብ 3 በመቶ ወደ 23 ነጥብ 6 በመቶ ማሳደግ እንደተቻለ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያን የተራቆተ የመሬት ገፅታ በደን በመሸፈን የአፈር መሸርሸርና የሥነ-ምኅዳር ደኅንነትን መጠበቅ ያስቻለ ውጤት እየተገኘ መሆኑንም አንስተዋል።

ቡናን ጨምሮ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር የሚተከሉ ችግኞች የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ ዘርፈ-ብዙ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ እያበረከቱ እንደሚገኙም አረጋግጠዋል።
በቀጣይም የማኅበረሰቡን የደን ጥበቃ ግንዛቤ በማሳደግና የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር በማስቀጠል በትኩረት እንደሚሠራ አመላክተዋል።
ሀዋሳ፤ ግንቦት 6/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ እየተከናወኑ ያሉ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች ከተረጅነት የመውጣት ጥረትን ለማሳካት የሚያስችል ተጨባጭ ውጤት እያመ...
May 15, 2026
ጅግጅጋ፤ ሚያዝያ 13/2018 (ኢዜአ)፦ በኦዲት ዘርፍ በተከናወኑ የሪፎርም ተግባራት ተጨባጭ ለውጦች እየተመዘገቡ መሆናቸውን የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሠረት ዳምጤ...
Apr 22, 2026
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 7/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በምግብ ዋስትና እና በኢኮኖሚ ልማት ዘርፍ እያከናወነቻቸው ያሉ ተግባራት ለመላው አፍሪካ አገራት ትልቅ አ...
Apr 16, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 24/2018 (ኢዜአ)፦ ሀገራዊ ለውጡ የሀገሪቱን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ስብራቶች በመጠገን፣ ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ከፍታና ለማህበራዊ ትስስ...
Apr 3, 2026