🔇Unmute
ድሬዳዋ፤ መጋቢት 12/2018 (ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ለአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ በተደረጉ የተቀናጁ ድጋፎች ወደ ማምረት የተመለሱ ኢንዱስትሪዎች ለበርካቶች የሥራ ዕድል መፍጠራቸው ተገለጸ።
የድሬዳዋ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባና የንግድ፣ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ ሀርቢ ቡህ ለኢዜአ እንዳሉት፤ ባለፉት አራት ዓመታት በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ለአምራች ኢንዱስትሪው በተደረገው ድጋፍና ክትትል በግንባታ ላይ እና ተዘግተው የነበሩ በርካታ ኢንዱስትሪዎች ከ10 ሺህ ለሚልቁ ጎች የሥራ ዕድል ፈጥረዋል።

ኢንዱስትሪዎቹ ተኪ ምርቶችን እና ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን በማምረት የውጭ ምንዛሬን የማዳንና የማስገኘት ዐቅማቸው እየጨመረ መምጣቱንም ተናግረዋል።
በሌላ በኩል በያዝነው የበጀት ዓመት ብቻ 11 ኢንዱስትሪዎች ተመርቀው ሥራ መጀመራቸውን ገልጸው፤ ፋብሪካዎቹ ከ1 ሺህ 500 በላይ ለሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠራቸውን አንስተዋል።
ከሁለት ወራት በኋላም ሥድስት ፋብሪካዎችን ወደ ሥራ ለማስገባት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አስታውቀዋል።

የፌደራልና የአሥተዳደሩ ተቋማት የተካተቱበት ዘርፉን የሚደግፍ አሠራር ተዘርግቶ፤ የኢንዱስትሪዎቹን የዓመታት የፋይናንስ፣ የመሬት፣ የመንገድ፣ የውኃ፣ የኃይልና የአገልግሎት ጥያቄዎችን በፍጥነት የመፍታት ተግባር እየተከናወነ መሆኑም አረጋግጠዋል።
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 24/2018 (ኢዜአ)፦ ሀገራዊ ለውጡ የሀገሪቱን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ስብራቶች በመጠገን፣ ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ከፍታና ለማህበራዊ ትስስ...
Apr 3, 2026
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025