የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

ዩኒቨርስቲው ለዲጂታል ኢትዮጵያ ስኬት በዘርፉ የተሻለ ክህሎት ያለው የሰው ኃይል ለማፍራት ድርሻውን እየተወጣ ነው

Mar 23, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ሮቤ፤ መጋቢት 12/2018 (ኢዜአ)፦ የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ለዲጂታል ኢትዮጵያ ስኬት በዘርፉ የተሻለ ክህሎት ያለው የሰው ኃይል ለማፍራት ድርሻውን እየተወጣ መሆኑን ገለጸ።

ዩኒቨርሲቲው ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በቴክኖሎጂ ፈጠራና ኢንተርፕረነርሺፕ ላይ ያተኮረ ተግባር ተኮር ሥልጠና እየሰጠ ይገኛል።

ይህ ሥልጠና ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ግብ ስኬት ጉልህ ድርሻ እንደሚኖረው ተመላክቷል።

የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዚዳንት በዛብህ ወንድሙ (ተባባሪ ፕሮፌሰር) እንደገለጹት፤ ዩኒቨርሲቲው በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ ብቁ ዜጎችን ለማፍራት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው።


በተለይም በባሌ እና ምስራቅ ባሌ ዞኖችና በምዕራብ አርሲ ዞን በሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የቴክኖሎጂ ዝንባሌ ያላቸውን ተማሪዎች በመመልመል የክህሎት ሥልጠና እንዲያገኙ እያደረገ ይገኛል ብለዋል።

ከዚህም ባለፈ በተለያዩ ጊዜያት በሚሰጡ የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎች የዜጎችን የሥራ ፈጣሪነት ባህል በሚያሳድግ መልኩ እንዲሰጡ መደረጉንም ገልጸዋል።


በ2017 ዓ.ም በሀገር አቀፍ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ውድድር ዩኒቨርሲቲውን ወክለው የቀረቡ ተማሪዎች አንደኛ ደረጃን በመያዝ ሽልማትና እውቅና ማግኘታቸው የዘርፉ ትኩረት ውጤት መሆኑን ለአብነት አንስተዋል።

በአሁኑ ወቅትም አዲስ የፈጠራ ሀሳብና ግኝት ያላቸው ግለሰቦች በሥራቸው ስኬታማ እንዲሆኑና ሊያጋጥሟቸው የሚችሉ ተግዳሮቶችን እንዲረዱ የአቅም ግንባታ ሥልጠና እየተሰጠ መሆኑን አክለዋል።

ዩኒቨርሲቲው ለዲጂታል ኢትዮጵያ ስኬት በዘርፉ ክህሎት የበለጸገ የሰው ኃይል ለማፍራት ድርሻውን መወጣቱን ይቀጥላል ነው ያሉት።

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የጀማሪ ሥራ ፈጣሪዎች ኢንተርፕራይዝ ከፍተኛ ባለሙያ ወይዘሮ ራሄል ደበበ በበኩላቸው፤ ዲጂታል ኢትዮጵያ አገልግሎትን ከማዘመን ባለፈ የዜጎችን ተወዳዳሪነት እንደሚያሳድግ ተናግረዋል።

ባለፉት ዓመታት በተከናወኑ ተግባራትም ተቋማት አገልግሎታቸውን ከቴክኖሎጂ ጋር በማስተሳሰር የዜጎችን ጊዜና ወጪ መቆጠብ መቻሉን አስታውሰዋል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተሻለ የፈጠራ ሀሳብ ያላቸው ወጣቶች ውጤታማ እንዲሆኑ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየሰራ መሆኑንና የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ መድረክም የዚሁ ጥረት አካል መሆኑን ገልጸዋል።


የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ሀገራዊ ለውጡ ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ከፍታና ማህበራዊ ትስስር ጠንካራ መሰረት የጣለ ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 24/2018 (ኢዜአ)፦ ሀገራዊ ለውጡ የሀገሪቱን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ስብራቶች በመጠገን፣ ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ከፍታና ለማህበራዊ ትስስ...

Apr 3, 2026

<p>ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በቦንጋ ከተማ የተለያዩ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው</p>

ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...

Feb 24, 2025

<p>በክልሉ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ እየተካሄደ ነው</p>

ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...

Feb 24, 2025

<p>በሚቀጥሉት አምስት አመታት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይት በተሻለ መልኩ ስራ ላይ ይውላል - የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...

Feb 8, 2025