የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

ፕሮጀክቶቹ ኢትዮጵያን የአፍሪካ የብልፅግና ተምሳሌት የማድረግ ራዕይን የሚያሳኩ ናቸው

Dec 2, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 22/2018(ኢዜአ)፦ የጉባ ብስራት ግዙፍ ብሔራዊ ፕሮጀክቶች የኢንዱስትሪ ልህቀትን በማሳደግ ኢትዮጵያን የአፍሪካ የብልፅግና ተምሳሌት የማድረግ ሀገራዊ ራዕይን የሚያሳኩ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጳጉሜን 4/2017 ዓ.ም ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ሲመርቁ በጉባ ሰማይ ስር የ30 ቢሊየን ዶላር ግዙፍ ብሔራዊ ፕሮጀክቶችን ማብሰራቸው ይታወቃል።

በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተበሰሩት የኢትዮጵያ ግዙፍ ብሔራዊ ፕሮጀክቶችም ሰላማዊ የኒውክሌር ማብላያ፣ የነዳጅ ዘይት ማጣሪያ፣ የተፈጥሮ ጋዝ ፋብሪካ፣ ግዙፍ የአየር ማረፊያ፣ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ቤቶችና የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ ናቸው።


የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል፤ የጉባ ብስራት ብሔራዊ ፕሮጀክቶች የኢትዮጵያን መፃኢ የብልጽግና ዕድል የሚወስኑ ግዙፍ የልማት ግቦች መሆናቸውን ገልጸዋል።

በተለይም የዘርፎችን እመርታዊ ሽግግር በማፋጠን ኢትዮጵያ የሚጠይቃትን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ወጪ በማስቀረት የሀገር ውስጥ ተኪ ምርታማነት አቅምን ለማሻሻል አይነተኛ ሚና እንደሚኖራቸው ተናግረዋል።

የአፈር ማዳበሪያና የተፈጥሮ ጋዝ ፋብሪካዎቹም የኢትዮጵያን የግብርና ምርታማነት በማሻሻል የኢንዱስትሪ ሽግግርን በማፋጠን የምግብ ሉዓላዊነትንና የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱ አብራርተዋል።

የነዳጅ ዘይት ማጣሪያ ፋብሪካው እና ሰላማዊ የኒውክሌር ማብላያ ፕሮጀክቶችም ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሃብቷን ተጠቅማ ዕድገትና ብልጽግናዋን ማረጋገጥ የሚያስችል አስተማማኝ የኃይል አቅም እንድትገነባ ያስችላሉ ብለዋል።


ኒውክሌርን ለሰላማዊ ዓላማ የማዋል ግብ በሁሉም መስክ የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪና የቴክኖሎጂ ሽግግር እንደሚያፋጥን ጠቅሰዋል።

የጉባ ብስራት የ30 ቢሊየን ዶላር ብሔራዊ የልማት ፕሮጀክቶችም በሁሉም መስክ ኢትዮጵያን የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት የማድረግ ሀገራዊ ራዕይን የሚያሳኩ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ሀገራዊ ለውጡ ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ከፍታና ማህበራዊ ትስስር ጠንካራ መሰረት የጣለ ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 24/2018 (ኢዜአ)፦ ሀገራዊ ለውጡ የሀገሪቱን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ስብራቶች በመጠገን፣ ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ከፍታና ለማህበራዊ ትስስ...

Apr 3, 2026

<p>ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በቦንጋ ከተማ የተለያዩ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው</p>

ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...

Feb 24, 2025

<p>በክልሉ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ እየተካሄደ ነው</p>

ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...

Feb 24, 2025

<p>በሚቀጥሉት አምስት አመታት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይት በተሻለ መልኩ ስራ ላይ ይውላል - የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...

Feb 8, 2025