የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የልማት ዕቅዶች ትግበራ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋገጠ

Oct 15, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ጥቅምት 4/2018 (ኢዜአ)፡-ለኢትዮጵያ የልማት ዕቅዶች ትግበራ እያደረገ ያለውን ዘርፈ ብዙ ድጋፍ በቀጣይም በተለያዩ መስኮች አጠናክሮ እንደሚቀጥል ዓለም ባንክ አረጋግጧል።

በገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ የተመራ ከፍተኛ ልዑክ በዓለም ባንክ የምሥራቅ እና ደቡብ አፍሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት ንዲያሜ ዲዮፕ ጋር ውጤታማ ውይይት አድርጓል።


በውይይቱ ላይ የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)፣የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማክሮ ኢኮኖሚ ከፍተኛ አማካሪ ተክለወልድ አጥናፉን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት ተገኝተዋል።

በውይይታቸውም፥ ሁለቱ ወገኖች በኢትዮጵያ እየተካሄደ ስላለው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ፣ የፕሮጀክቶች ሂደት እና ለቀጣይ በሚኖሩ ዋና ዋና የትብብር ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

አቶ አሕመድ በዚሁ ወቅት የዓለም ባንክ የኢትዮጵያን የልማት አጀንዳ በማሳደግ ረገድ ያለውን ወሳኝ ሚና አንስተው፥ለተደረገው እና በቀጣይም ለሚደረገው ከፍተኛ የቴክኒክ እና የገንዘብ ድጋፍ አመሥግነዋል።

ሰው ተኮርና ድህነት ቅነሳ ላይ እየተከናወኑ ስላሉ ውጤታማ ሥራዎች፣ በግብርና ምርታማነት፣ በኢነርጂ፣በሰብዓዊ ካፒታል ልማት እና በመሠረተ ልማት ዘርፎች የላቀ እገዛ እንደሚያስፈልግም አስገንዝበዋል።

ንዲያሜ ዲዮፕ በበኩላቸው፥ የኢትዮጵያ መንግሥት ለልማት እያሳየ ያለውን ቁርጠኛ አመራር እና አጠቃላይ ሂደት አድንቀዋል።


በመንግሥት ቁርጠኝነትም ሁሉን አቀፍ ማሻሻያ ፕሮግራም በጀመረ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወሳኝ የሆኑ የማክሮ ኢኮኖሚ ግቦችን ማሳካት መቻሉን አንስተዋል።

በቀጣይም የዓለም ባንክ የኢትዮጵያን የልማት ዕቅዶች በተለያዩ መስኮች ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል።

በዚህም መሠረት በኢነርጂ፣በግብርናና የአነስተኛ አርሶ አደሮች ምርታማነት፣ የፋይናንስ አቅርቦት እና የእሴት ሰንሰለት ልማትን ለማሳደግ ዓለም ባንክ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

በተጨማሪም የሀገር ውስጥ ማኑፋክቸሪንግ ተነሳሽነትን እና የሀገር ውስጥ ምርትን ማሳደግ በሚሉት እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ድጋፉን እንደሚያጠናክር ነው የገለጹት።

የኢትዮጵያ የልማት መርሐ ግብሮች፣ የሀገሪቱ የእድገትና የዘላቂ ልማት ዋና ዋና አንቀሳቃሾች በተሳካ ሁኔታ ተፈፃሚ እንዲሆኑ የሁሉም አጋር አካላት ቀጣይነት ያለው ድጋፍ አስፈላጊ መሆኑን በማረጋገጥ ለቀጣይ ትብብር ያላቸውን ቁርጠኝነት ለማስቀጠል መግባባት ላይ ተደርሷል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ሀገራዊ ለውጡ ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ከፍታና ማህበራዊ ትስስር ጠንካራ መሰረት የጣለ ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 24/2018 (ኢዜአ)፦ ሀገራዊ ለውጡ የሀገሪቱን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ስብራቶች በመጠገን፣ ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ከፍታና ለማህበራዊ ትስስ...

Apr 3, 2026

<p>ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በቦንጋ ከተማ የተለያዩ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው</p>

ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...

Feb 24, 2025

<p>በክልሉ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ እየተካሄደ ነው</p>

ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...

Feb 24, 2025

<p>በሚቀጥሉት አምስት አመታት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይት በተሻለ መልኩ ስራ ላይ ይውላል - የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...

Feb 8, 2025