የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

በሲዳማ ክልል ከ80 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ ይለማል

Sep 30, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

‎ሀዋሳ፤ መስከረም 19/2018 (ኢዜአ) :- በሲዳማ ክልል በዘንድሮው በጋ ከ80 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ እንደሚለማ የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ገለፀ ።

‎በሲዳማ ክልል የ2018 የምርት ዘመን የበጋ መስኖ ልማት የንቅናቄ መድረክ ተካሄዷል።

‎የቢሮው ኃላፊ አቶ መምሩ ሞኬ እንደገለፁት በክልሉ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና ገበያን ለማረጋጋት ለመስኖ ልማት ሥራ ትኩረት መሰጠቱን ተናግረዋል፡፡


ይህም ባለፉት ዓመታት በመስኖ የሚለማ መሬት ሽፋንን በማሳደግ የምርት መጠን እንዲጨምር መደረጉን ገልፀዋል፡፡

ለአብነትም ባለፈው ዓመት በበጋ መስኖ 73 ሺህ ሄክታር መሬት ማልማት እንደተቻለ ጠቅሰው ይህንንም በዘንድሮው በጋ ከ80 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ለማሳደግ መታቀዱን ጠቁመዋል ።

አርሶ አደሩ የመስኖ አውታሮችን ለማልማት ኩሬዎችን፣ አነስተኛ ጉድጓዶችን፣ ጅረቶችንና ወንዞችን ጨምሮ ሁሉንም የውሃ አማራጭ ተጠቅሞ በማልማት ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ በዓመት ሁለትና ሶስት ጊዜ ማምረት እንዲችል እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል ፡፡

የክልሉ መንግስት ዝናብ አጠር በሆኑ አካባቢዎች ላይ ከፍተኛ በጀት በመመደብና ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶችን በመቆፈር ከዚህ ቀደም በመስኖ ልማት የማይታወቁ አካባቢዎች ጭምር ዓመቱን ሙሉ እንዲያመርቱ ማድረግ መቻሉን ገልፀዋል፡፡


የቢሮው ምክትልና የእርሻ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ባንጉ በቀለ በበጋ የመስኖ ልማት ከ80 ሺህ 55 ሄክታር በላይ መሬት በማልማት ከ18 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት መታቀዱን አስረድተዋል፡፡

ከመስኖ ልማቱም ከ24 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆነው መሬት በኩታ ገጠም የሚለማ መሆኑን ጠቁመው በዚህ የልማት ሥራም ከ350 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑም ጠቅሰዋል፡፡

ምርጥ ዘር፣ የአፈር ማዳበሪያ እንዲሁም ሌሎች ግብዓቶች በበቂ ሁኔታ ለአርሶ አደሩ እንዲደርሱ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል፡፡

በንቅናቄ መድረኩ ላይም የክልሉ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ሀገራዊ ለውጡ ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ከፍታና ማህበራዊ ትስስር ጠንካራ መሰረት የጣለ ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 24/2018 (ኢዜአ)፦ ሀገራዊ ለውጡ የሀገሪቱን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ስብራቶች በመጠገን፣ ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ከፍታና ለማህበራዊ ትስስ...

Apr 3, 2026

<p>ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በቦንጋ ከተማ የተለያዩ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው</p>

ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...

Feb 24, 2025

<p>በክልሉ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ እየተካሄደ ነው</p>

ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...

Feb 24, 2025

<p>በሚቀጥሉት አምስት አመታት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይት በተሻለ መልኩ ስራ ላይ ይውላል - የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...

Feb 8, 2025