የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የህዝቡን ፍትሃዊ የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው -- ርእሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ

Jul 3, 2025

IDOPRESS

ወላይታ ሶዶ፤ ሰኔ 25/2017 (ኢዜአ) --በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የህዝቡን ፍትሃዊ የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ገለጹ፡፡

የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት የ2018 ዓ.ም በጀት ማከፋፈያ ቀመር ሂደት ላይ ተግባቦት ለመፍጠር ያለመ የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ ተካሂዷል፡፡


የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ በዚህ ወቅት እንደገለጹት በክልሉ ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል እና የልማት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራት በትኩረት እየተከናወኑ ነው።

የክልሉን ህዝብ አዳጊ ፍላጎቶችን ለማሟላት እና ፍትሃዊ የልማት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በበጀት ቀመር ላይ ተግባቦት መፍጠር እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል።

በዚህም የ2018 ዓ.ም በጀት ከመወሰኑ በፊት ከተለያዩ ምንጮች የተሰበሰቡ መረጃዎችን መሰረት በማድረግ የበጀት ቀመሩን ለመስራት መግባባት ላይ መድረስ በማስፈለጉ መድረኩ መዘጋጀቱን ገልጸዋል።

የክልሉ ብሄረሰቦች ምክር ቤት በበጀት ቀመሩ ላይ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ማከናወኑን ጠቅሰው መግባባት የተደረሰበት መረጃ ለክልሉ ምክር ቤት ይቀርባል ብለዋል፡፡


የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አዳማ ቲምጳዬ በበኩላቸው በ2018 በጀት ዓመት ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍልና የልማት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ መረጃዎችን የማደራጀት ስራ መሰራቱን ገልጸዋል።

መድረኩ በሁሉም መዋቅር አመራሮች ዘንድ ግልጽነትና መግባባት በመፍጠር የኢኮኖሚን አቅምን መሠረት ያደረገ የበጀት ቀመር ተግባራዊ ለማድረግ የሚያግዝ ነው ብለዋል፡፡

ግልጽና ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል እንዲኖር የ2018 በጀት ቀመር የማዘጋጀትና የማደራጀት ስራ ሲሰራ መቆየቱን የተናገሩት ደግሞ የክልሉ ፕላን እና ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፈቃደስላስ ቤዛ ናቸዉ።

የዘንድሮውን የበጀት ቀመር የማዘጋጀቱ ስራ እየተገባደደ ባለው በጀት ዓመት የተስተዋሉ ችግሮችን በመቅረፍ ለበጀት ቀመር ዝግጅት መረጃዎችን የማናበብና የማጥራት ተግባር የተከናወነበት መሆኑንም ገልጸዋል።

ለዚህም ስራ ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ ያሉ የሶስት ዓመት መረጃዎችን የማመሳከር ስራ መሰራቱንም አክለዋል።

በመድረኩ የክልል፣የዞኖች እና የ3ቱ ሪጂዮፖሊስ ከተሞች ባለድርሻዎች ተገኝተውበታል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ሀገራዊ ለውጡ ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ከፍታና ማህበራዊ ትስስር ጠንካራ መሰረት የጣለ ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 24/2018 (ኢዜአ)፦ ሀገራዊ ለውጡ የሀገሪቱን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ስብራቶች በመጠገን፣ ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ከፍታና ለማህበራዊ ትስስ...

Apr 3, 2026

<p>ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በቦንጋ ከተማ የተለያዩ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው</p>

ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...

Feb 24, 2025

<p>በክልሉ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ እየተካሄደ ነው</p>

ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...

Feb 24, 2025

<p>በሚቀጥሉት አምስት አመታት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይት በተሻለ መልኩ ስራ ላይ ይውላል - የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...

Feb 8, 2025