🔇Unmute
አሶሳ፤ መጋቢት 9/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለመኸር እርሻ የሚሆን የአፈር ማዳበሪያ በወቅቱ ተደራሽ እየተደረገ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።
በክልሉ ግብርና ቢሮ የግብዓት አቅርቦት ዳይሬክተር ተስፋዬ በቀለ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ በክልሉ ለዘንድሮው የመኸር እርሻ የሚውል 131 ሺህ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ ተደራሽ ለማድረግ ታቅዷል።
እስከአሁን ድረስም 98 ሺህ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ በአሶሳ ከተማ እና መተከል ዞን በሚገኙ ማከማቻ መጋዘኖች እንደሚገኝ ገልጸዋል።
የአፈር ማዳበሪያው በወቅቱ መድረሱ አርሶ አደሩ የመኸር እርሻ ዝግጅቱን ከመጀመሩ በፊት የአፈር ማዳበሪያ ግዢ እንዲያከናውን ጊዜ የሚሰጥ መሆኑንም ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።
የአፈር ማዳበሪያ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የአርሶ አደሩን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እያሳደገ መሆኑን የገለፁት ዳይሬክተሩ የአርሶ አደሩ የአፈር ማዳበሪያ ፍላጎት እየጨመረ መሆኑን ገልጸዋል።
ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ በየወረዳው በተደለደለው ኮታ መሠረት አርሶ አደሩ የአፈር ማዳበሪያውን እንደሚወስድ ተናግረዋል።
ከአርሶ አደሩ በተጨማሪ በትልልቅ የእርሻ ኢንቨስትመንት የተሰማሩ ባለሃብቶች የአፈር ማዳበሪያ እንዲያገኙ በማድረግ በክልሉ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አክለዋል።
ከአፈር ማዳበሪያ በተጨማሪ የምርጥ ዘር ግብዓት በቅርቡ ወደ ክልሉ እንደሚገባም አረጋግጠዋል።
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የውጭ ቀጥታ ንግድና ኢንቨስትመንት ስኬት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ተግባራዊ ውጤት ማሳያ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ...
Mar 27, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የብዝኅ ኢኮኖሚ ልማት የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ በማሳደግ አህጉራዊ የኢንቨስትመንት ማዕከልነትን እያረጋገጠ ...
Mar 26, 2026
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025