🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የብዝኅ ኢኮኖሚ ልማት የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ በማሳደግ አህጉራዊ የኢንቨስትመንት ማዕከልነትን እያረጋገጠ እንደሚገኝ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አሕመድ ሽዴ ገለጹ፡፡
የመጀመሪያው የኢትዮ-ጣሊያን የኮንስትራክሽን፣ የመሰረተ ልማትና የከተማ ልማት ፎረም በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡

በዚሁ ወቅት የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አሕመድ ሽዴ፤ የኢትዮጵያ ሀገር በቀል የሪፎርም እርምጃ ዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ተወዳዳሪነትን በማሳደግ አስቻይ ሁኔታን ፈጥሯል ብለዋል።
የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውም የኢትዮጵያና ጣሊያንን የንግድና ኢንቨስትመንት ትብብር በማሳደግ በኃይልና በከተማ ልማት እመርታዊ ውጤት እያስገኘ መሆኑን ገልጸዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የጣሊያን አቻቸው አመራር ሰጪነትም የሀገራቱን የሁለትዮሽና ባለብዙ ወገን የዲፕሎማሲ ትብብር በማጠናከር ጉልህ ሚና እየተወጣ መሆኑን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ማበረታቻ የመሠረተ ልማትና የአሰራር ሥርዓትም አዲስ አበባን ዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ተመራጭነት እያጎለበተ እንደሚገኝ አንስተዋል።
የኢትዮጵያ የህዝብ ቁጥር፣ ሰፊ የገበያ ዕድልና የመንግስት ቁርጠኝነትም ቀጣናዊ የኢንቨስትመንት መዳረሻ የመሪነት ሚናዋን አጠናክራ እንድትቀጥል እያስቻላት መሆኑን ገልጸዋል።
ለብዝኅ የኢኮኖሚ ዘርፍ የተሰጠው ትኩረትም የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ በማሳደግ ኢትዮጵያን አፍሪካዊት የንግድና ኢንቨስትመንት የስበት ማዕከል እያደረጋት መሆኑን ተናግረዋል።
በቀጣይም ኢትዮጵያ ከጣሊያን ጋር ያላትን ትብብር በማጠናከር ለቀጣናዊ ልማት፣ ሰላምና ደኅንነት በቁርጠኝነት እንደምትሰራ አረጋግጠዋል።

የጣሊያን የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ምክትል ሚኒስትር ማሪያ ትሪፖዲ በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያና ጣሊያን የሁለትዮሽ ግንኙነት በጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት የተመሠረተ ነው ብለዋል።
የኢትዮጵያና ጣሊያን የታዳሽ ኃይል ልማት አቅምና የካበተ ልምድም ለሀገራቱ ትብብር ወሳኝ መሰረት መሆኑን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሥርዓት ለውጭ ኢንቨስትመንት ክፍት መደረጉም ለጣሊያንና ዓለም አቀፍ አልሚዎች ምቹ መደላድል መፍጠሩን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በምታካሂዳቸው የታዳሽ ኃይል፣ ሎጀስቲክስ፣ የአየር መንገድና መሰል መሠረተ ልማት ግንባታ ሥራዎች በጣሊያን የማቴ ዕቅድ መሰረት ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል።
ሰመራ፤ ግንቦት 12/2018(ኢዜአ)፦በአፋር ክልል ለህብረተሰቡ የዘመናት ጥያቄ ምላሽ የሚሰጡ ፕሮጀክቶች ለአገልግሎት እየበቁ መሆናቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
May 21, 2026
ወላይታ ሶዶ፤ ሚያዝያ 21/2018 (ኢዜአ)፦ በወላይታ ሶዶ ከተማ ከነዳጅ እጥረት ጋር በተያያዘ በህዝብ የትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የነበረውን ክፍተት ለማረም...
Apr 30, 2026
ጅማ፤ ሚያዝያ 21/2018(ኢዜአ)፦ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የምርምር ሥራዎቻቸውን ከቀጣናዊ ተጨባጭ ሁኔታዎች ጋር በማስተሳሰር ዘላቂ ሰላምና የጋራ እድገት ለ...
Apr 30, 2026
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 20/2018(ኢዜአ)፦የትራንስፖርት አገልግሎትን ከነዳጅ ጥገኝነት ለማላቀቅ ተግባራዊ የተደረጉ ስልቶች ተጨባጭ ውጤት እያመጡ መሆኑን የትራን...
Apr 29, 2026