የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

‎በሲዳማ ክልል በሞዴል መንደሮች ግንባታ የገጠሩን ማህበረሰብ ኑሮ ለማሻሻል የተጀመረው ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል

Mar 9, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

‎ሀዋሳ፤ የካቲት 29/2018(ኢዜአ)፦ ‎በሲዳማ ክልል ሞዴል መንደሮችን በማስፋፋት የገጠሩን ማህበረሰብ ሕይወት ለማዘመን የተጀመረው ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ገለጹ።

የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማቱ ጋር በመተባበር ያስገነባው ዘመናዊ የገጠር መንደር በሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ እና በፕላንና ልማት ሚኒስትሯ ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) ተመርቋል።

በክልሉ ዳራ ወረዳ መጪሾ ቀበሌ የተገነባ ሞዴል መንደር አቅመ ደካማ ቤተሰቦችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው።

በምረቃ መርሀግብሩ ላይ የተገኙት የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ እንዳሉት በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች ሞዴል መንደሮችን በማስፋፋት ህብረተሰቡ የተሻለ ኑሮ እንዲኖረው ለማድረግ እየተሰራ ነው።

‎በመንደሩ የተገነቡት ቤቶች ዘመናዊ ከመሆናቸው ባለፈ የስልጡን ማህበረሰብ መስፈርቶችን ያሟሉ በመሆናቸው ብልጽግናን በሁሉም አካባቢዎች ለማድረስ የሚደረጉ ጥረቶች ማሳያ ናቸው ብለዋል።

የመደመር መንግሥት የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑን አንስተው የመጪሾ ሞዴል የገጠር መንደርም የዚሁ ጥረት ውጤት መሆኑን ገልፀዋል።

‎በክልሉ ዛሬ ከተመረቀው በተጨማሪ የግንባታ ስራ የተጀመረባቸው ወረዳዎች እንዳሉና ተስፋፍቶ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።

‎የአርሶ አደሩን የኢኮኖሚ አቅም ከማሳደግ ባለፈ ዘመናዊ ሕይወት እንዲኖረው ለማድረግ ትኩረት መሰጠቱን የገለጹት አቶ ደስታ፣ የሌማት ትሩፋትን ጨምሮ የግብርናን ምርታማነት ለማሳደግ በተሰራው ስራ ውጤት መገኘቱን ተናግረዋል።

‎የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) በበኩላቸው ሞዴል መንደሩ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የገጠር ኮሪደር ልማት እሳቤ በመነሳትና ቀደም ተብሎ ከተሰሩ ልማቶች ልምድ በመውሰድ የተገነባ መሆኑን ጠቅሰዋል።

‎ቤቶቹ የውሃ፣ የፀሐይና የባዮ ጋዝ ኃይል ያላቸው መሆኑን ጠቅሰው፤ የወተት፣ የዶሮና ሌሎች የሌማት ቱሩፋት ሥራዎችን ለማከናወን የሚያስችሉ ግንባታዎችን ያካተቱ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

ሞዴል መንደሮቹ የገጠሩን ማህበረሰብ አኗኗር ወደዘመናዊነት ለመቀየር የሚያስችሉ መሆናቸውን ገልፀው፤ በሁሉም አካባቢ መስፋት እንዳለባቸው አመልክተዋል።

የመደመር መንግስት የገጠር አካባቢ ነዋሪዎችም ዘመናዊ አኗኗርን እንዲከተሉ በትኩረት እየሰራ ስለመሆኑ አንስተው በቀጣይም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።

‎በሞዴል መንደሩ አምስት ዘመናዊ ቤቶች የተገነቡ ሲሆን እያንዳንዳቸው በ1ሺህ 200 ካሬ ሜትር ላይ ያረፉ እንደሆኑም ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኢትዮጵያ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ስኬት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ተግባራዊ ውጤት ማሳያ ነው

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የውጭ ቀጥታ ንግድና ኢንቨስትመንት ስኬት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ተግባራዊ ውጤት ማሳያ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ...

Mar 27, 2026

የኢትዮጵያ የብዝኅ ኢኮኖሚ ልማት የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ በማሳደግ የኢንቨስትመንት ማዕከልነት እያረጋገጠ ነው

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የብዝኅ ኢኮኖሚ ልማት የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ በማሳደግ አህጉራዊ የኢንቨስትመንት ማዕከልነትን እያረጋገጠ ...

Mar 26, 2026

<p>የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው ጉዳይ አይደለም- ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...

Feb 28, 2025

<p>የባለፉት ዓመታት ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት አሳድገዋል</p>

ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...

Feb 24, 2025