የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

በሀገሪቱ የቡና ምርት ጥራት ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ የቅምሻ ባለሙያዎችን ማፍራት ላይ ትኩረት ተደርጓል

Feb 13, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ሀዋሳ ፤ የካቲት 5/2018(ኢዜአ)፦በሀገሪቱ የቡና ምርት ጥራት ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ የቅምሻ ባለሙያዎችን ማፍራት ላይ ትኩረት መደረጉን የኢትዮጵያ ምርት ገበያ አስታወቀ።

ምርት ገበያው ዘመናዊና ጥራት ላይ ያተኮረ ግብይትን ለማሳለጥ ያለመ የሰው ኃይል ለማፍራት አካዳሚ ከፍቶ እየሰራ ነው።

ዛሬ በሀዋሳ ማዕከል የተጀመረው የመጀመሪያ ዙር ስልጠናም የቡና ቅምሻ ደረጃ አወጣጥ ላይ ማተኮሩ ተመልክቷል።

የምርት ገበያው አካዳሚ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን ተሾመ፤ ምርት ገበያው ቡናን ጨምሮ የግብርና ምርቶች ግብይትን በማዘመን ጥራታቸውን እንዲጠብቁ ለማድረግ ለክህሎት ስልጠና ትኩረት በመስጠት እየሰራ ነው ብለዋል።

በዚህም የቡና መገኛ የሆነችው ኢትዮጵያ የሚገባትን ለማግኘት፣ በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪነቷን ለማጠናከርና የምርት ሂደቱ የጥራት ደረጃውን እንዲጠብቅ ለማድረግ በዕውቀት የሚሰራ የሰው ኃይል ለማፍራት ጥረት እየተደረገ መሆኑን አንስተዋል።

የዓለም አቀፍ ገበያው የሚፈልገውን የጥራት ደረጃ የሚመጥን ምርት ለማውጣትና በድህረ ምርት ሂደት ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመቅረፍ በክህሎት የዳበረ የሰው ሀይል ማብቃት አስፈላጊ መሆኑን አመልክተዋል።


መሰል ስልጠና በአዲስ አበባ ማእከል ከተጀመረ ሶስት ዓመታት እንዳስቆጠረ ገልፀው በዚህም 480 ባለሙያዎች መሰልጠናቸውንና ስልጠናውን በማስፋት ዛሬ በሀዋሳ መጀመሩንም ጠቁመዋል።

ሀገሪቱ ከወጭ ንግድ የሚገባትን እንድታገኝ በዘርፉ የሰለጠነ የሰው ሀይል ማፍራት እንደሚገባ የገለጹት ደግሞ በምርት ገበያው የሀዋሳ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅና የቡና ጥራት ባለሙያ አቶ ነቢያት ጀማል ናቸው።

የሀዋሳ ስልጠና ማዕከልም በመጀመሪያው ዙር 27 ሰልጣኞችን ተቀብሎ በቡና ምርት ጥራት ማስጠበቅ ላይ የክህሎት ስልጠና እየሰጠ ነው ብለዋል።

ከሰልጣኞች መካከል ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ሀምበላዋመና ወረዳ የመጡት አቶ ድልነሣ አያልነህ፤ በቡና ልማት ዘርፍ ልምዱ ያላቸው ቢሆንም ከጥራት አንጻር የሚነሳውን ችግር ለመፍታት በስልጠናው እየተሳተፉ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

በተለይም በምናመርተው ልክ ተጠቃሚ ለመሆን የዓለም አቀፍ ገበያው የሚፈለገውን ጥራት ደረጃ ማሟላት ይገባል ያሉት ሰልጣኙ ለዚህ ደግሞ የምርት ገበያው የጀመረው ስልጠና ክህሎታቸውን በማዳበር እንደሚያግዛቸው ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኢትዮጵያ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ስኬት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ተግባራዊ ውጤት ማሳያ ነው

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የውጭ ቀጥታ ንግድና ኢንቨስትመንት ስኬት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ተግባራዊ ውጤት ማሳያ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ...

Mar 27, 2026

የኢትዮጵያ የብዝኅ ኢኮኖሚ ልማት የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ በማሳደግ የኢንቨስትመንት ማዕከልነት እያረጋገጠ ነው

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የብዝኅ ኢኮኖሚ ልማት የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ በማሳደግ አህጉራዊ የኢንቨስትመንት ማዕከልነትን እያረጋገጠ ...

Mar 26, 2026

<p>የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው ጉዳይ አይደለም- ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...

Feb 28, 2025

<p>የባለፉት ዓመታት ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት አሳድገዋል</p>

ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...

Feb 24, 2025