🔇Unmute
ባሕር ዳር ፤ ታህሳስ 2/2018(ኢዜአ)፡- ባሕር ዳር ከተማን ተመራጭ የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም መዳረሻ ማዕከል ማድረግ የሚያስችሉ የልማት ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማ አስተዳደሩ የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ ብርሃን ንጉሴ ገለጹ።
የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደርና የሰሜን ጎጃም ዞን ሰልጣኝ መካከለኛ አመራሮች በከተማዋ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው።

አመራሮቹ የኢንዱስትሪ መንደርን፣ የኮሪደር ልማት፣ የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዮም፣ መሶብ የአንድ ማዕከል የአገልግሎት መስጫና ሌሎች የመሰረተ ልማት ስራዎችን ተዘዋውረው እንደሚጎበኙም ታውቋል።
የመምሪያው ኃላፊ ወይዘሮ ብርሃን ንጉሴ በጉብኝቱ ወቅት እንዳሉት፤ ባሕር ዳርን ለነዋሪዎቿ ምቹና ፅዱ ከተማ ለማድረግ የተለያዩ የልማት ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።
በተለይ በከተማ አስተዳደሩ 268 የተለያዩ ኢንዱስትሪዎች በስራ ላይ እንዳሉ ጠቅሰው፤ 108 ኢንዱስትሪዎች ደግሞ በግንባታ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
እነዚህ ኢንዱስትሪዎች ተኪ ምርቶችን ከማምረት ባለፈ ለበርካታ ወገኖች የስራ ዕድል በመፍጠር የኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸውን በማረጋገጥ ሚናቸውን እየተወጡ ይገኛል ነው ያሉት።
እንዲሁም በመጀመሪያው ምዕራፍ የተገነባው የኮሪደር ልማት ከጣና ኃይቅ ጋር የሚያስተሳስሩ መንገዶች በመከፈታቸው የከተማዋ ውበት ይበልጥ የተገለጠበት መሆኑን ተናግረዋል።
እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች ከተማዋ ተመራጭ የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም መዳረሻ እንድትሆን እያስቻሉ መሆናቸውን አብራርተዋል።
በቀጣይም የተጀመሩ የልማት ስራዎችን በመደመር መንግስት እይታ በመቃኘት የከተማዋን ዕድገትና ልማት በማፋጠን የሕብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እንደሚሰራም አስታውቀዋል።
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የውጭ ቀጥታ ንግድና ኢንቨስትመንት ስኬት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ተግባራዊ ውጤት ማሳያ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ...
Mar 27, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የብዝኅ ኢኮኖሚ ልማት የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ በማሳደግ አህጉራዊ የኢንቨስትመንት ማዕከልነትን እያረጋገጠ ...
Mar 26, 2026
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025